top of page

ታህሳስ 16፣2017 በሰሜ ወሎ ዞን በተከሰተው ምግብ እጥረት ለተጎዱ ሰዎች አስቸኳይ የእለት ደራሽ ምግብ ያስፈልጋል ተባለ፡፡

#ሰሜ_ወሎ ዞን በተከሰተው ምግብ እጥረት ለተጎዱ 110,563 ሰዎች አስቸኳይ የእለት ደራሽ ምግብ ያስፈልጋል ተባለ፡፡


ለእነዚህ ተጎጂዎች ለመድረስ ለአንድ ዙር ብቻ 16,600 ኩንታል #የምግብ_ድጋፍ እንደሚስፈልግ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅህፈት ቤት ነግሮናል፡፡


ከዚህም ውስጥ በፌዴራሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በኩል 4,000 ኩንታል ያህሉ ወደ አካባቢው እየገባ መሆኑንና ለተጎጂዎች ማሰራጨት መጀመራቸውን የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አለሙ ይመር ነግረውናል፡፡


በሌላ በኩል ወደ አካባቢው እየተጓጓዘ ነው ከተባለው የምግብ እህል ቀደም ብሎ መድሃኒትና አልሚ ምግቦች የሞት አፋፍ ላይ የደረሱ ህፃናት ባሉባቸው ሁለት ወረዳዎች መሰረጨታቸውንም ሃላፊው ጨምረው ነግረውናል፡፡

በአማራ ክልል ባለው #የፀጥታ_ችግር ምክንያት ወደ ሰሜን ወሎ አካባቢ መውጣትም ይሁን መግባት ባለመቻሉ፤ለሁለት ወራት ያህል የእለት ደራሽ ድጋፍ ማድረግ ባለመቻሉ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ተከስቷል ብለዋል ሃላፊው፡፡


ይሁንና በአሁኑ ወቅት በሀገር ሽማግሌዎች አሸማጋነት አካባቢውን ከተቆጣጠረው ታጣቂ ቡድን ጋር ከስምምነት ላይ በመደረሱ ለተጎጂዎቹ መድረስ የጀመረው የእለት ደራሽ ምግብ ሳይቆራረጥ እንደሚቀጥል አቶ አለሙ ጠቅሰዋል፡፡


በተለይ በምግብ እጥረቱ የከፋ ጉዳት የደረሰባቸውን ህፃናት ወደ ስፍራው ገብተው የህክምናና የህይወት አድን ስራ እንዲሰሩ የተጠየቁት ግብረሰናይ ድርጅቶች ፍቃደኝነታቸውን አሳይተዋል ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/2vz6bune


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


bottom of page