top of page

ታህሳስ 15፣2017ኢትዮጵያ ወረራ ፈፅማብኛለች ስትል ሶማሊያ ከሰሰች፡፡የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ሀሰት ነው ብሏል፡፡

  • sheger1021fm
  • Dec 24, 2024
  • 1 min read



ትናንት፣ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር በትዊተር ገፁ ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ዶሎ በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊቴ ላይ ጥቃት ፈፀመችብኝ ብሏል፡፡


“የአንካራውን የሰላም ስምምነት በግልፅ ጥሳለች፤ ሲል የሚከሰው የሶማሊያ መግለጫ፣ ዶሎ ላይ ሆን ተብሎ እና በታቀደ መልኩ፣ በሶማሊያ ሰራዊት ፣  በብሔራዊ ደህንነት እና በፀጥታ ኤጀንሲው እንዲሁም በሶማሊያ የፖሊስ ሀይል ላይ ኢተዮጵያ ጥቃት ፈፅማለች” ይላል፡፡


የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ወረራ እንደፈፀመች ተደርጎ የወጣው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ብሏል፡፡


በኢትዮጵያና ሶማሊያ መንግስት የተፈረመው የአንካራው ስምምነት፣ ተግባራዊ እንዳይሆን የሚፈልጉና የአፍሪካን ቀንድ ለማተራመስ በሚፈልጉ አካላት የተፈፀመ ነው ሲል ለድርጊቱን 3ኛ ወገንን ተጠያቂ አድርጓል፡፡


ሶስተኛ ወገን ሲል የጠራቸውና ማንነታቸውን ያልገለፃቸው አካላት፣ ይህን እንዲያደርጉ መፈቀድ የለበትም”፣ ያለው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፣ ኢትዮጵያ አንካራውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅሷል፡፡


ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአንካራው ስምምነት ጋር ተያይዞ ሰላምን ለማበርታት በሶማሊያ የውጪ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኡመር የተመራ ልዑክ፣ ትላንት ኢትዮጵያ ገብቷል፡፡


የአንካራው ስምምነት ለማጠናከር የሚረዳ ውይይት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀላፊዎች ጋር ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡


በሌላ በኩል፣ በውጪ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትሩ አህመድ ሞአለም ፈቂ የተመራ ሌላ የሶማሊያ ልዑክ ወደ ግብፅ መሄዱ ተሰምቷል፡፡


ከሁለቱ ሚኒስትሮች ንግግር በኋላ፣ ግብፅ በአፍሪካ ህብረት ስር የሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ለመላክ የሁለቱም ሃገሮች ፍላጎት መሆኑን የጋራ መግለጫ መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page