top of page

ታህሳስ 14፣2017 - በኢትዮጵያ ከ5,200 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቢኖሩም ብዙዎቹ ግጭት ወዳለባቸው ቦታዎች ገብተው የመስራት ፍላጎት የላቸውም ሲል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተናገረ

Updated: Dec 25, 2024

በኢትዮጵያ ከ5,200 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቢኖሩም ብዙዎቹ ግጭት ወዳለባቸው ቦታዎች ገብተው የመስራት ፍላጎት የላቸውም ሲል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተናገረ።


በሀገሪቱ በሰላም ግንባታ ዙሪያ እንሰራለን በሚል የተመዘገብ የበዙ ድርጅቶች ቢኖሩም ብዙዎቹ ሰላም ባልሰፈነባቸው ቦታዎች ገብተውና ሀላፊነት ወስደው የመስራት ፍላጎት እንደሌላቸው ተነግሯል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ ''የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ግጭት ባለባቸው ቦታዎች የጀመሯቸው ፕሮጀክቶች ጭምር አቋርጠው ይወጣሉ'' ብለዋል።


ነገር ግን ድርጅቶቹ ባስቸጋሪ ሁኔታው ውስጥም ገብተው የመስራት ''የሞራልም የህግም ግዴታ አለባቸው'' ሲሉ ተናግረዋል።

ሀላፊው ይህንን የተናገሩት ጅረት የእርቅ እና ሰላም የተሰኘ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፣ ከአሜሪካ ፍሬንድስ ሰርቪስ ኮሚቴ ጋር በመተባበር #ግጭት ባሉባቸው አካባቢዎች የአእምሮ ቁስለትን ማከም በተመለከተ ከባድርሻዎች ጋር ለመምከር ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።


የጅረት ድርጅት ዳይሬክተር ዳዊት ደመቀ በተለይ በሰላም ግንባታ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች ችግር ወዳለባቸው ቦታዎች ገብተው መስራት እንደሚገባቸው አንስተዋል።


በሀገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች የተለያዩ በደሎች ለደረሰባቸው ማህበረሰቦች ስለ ሽግግር ፍትህ እና ሌሎች የግጭት አፈታት ስርዓቶች በብርቱ በማስገንዘብ ለሰላም እና እርቅ እንዲዘጋጁ ያስፈልጋልም ሲባል ሰምተናል።


ዘገባውን በድምፅ ያድምጡ


ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በምህረት ስዩም



댓글


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page