top of page

ታህሳስ 14፣2017 - በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ስደት ከሚወጡት ኢትዮጵያውያን መከከል 95 በመቶው ከአማራ፣ ከትግራይ እና ከኦሮሚያ ነው ተባለ።

ከዚህ ውስጥም 57 በመቶ ከአማራ ክልል እንደሚሄዱ ተነግሯል።


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገራቸው የሚወጡ የወንዶች ቁጥር ከፍ ማለቱን አረጋግጫለሁ ያለው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እድሜአቸውም ከ14 እስከ 30 ዓመት የሚሆኑ ናቸው ብሏል።


ለምን ወጣቶች እንዲህ በይፋ ይሰደዳሉ የሚለውን ጉዳይ በተመለከተም ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ፍሪደም ፈንድ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ያደረገውን ጥናት እያቀረበ ነው፡፡


በህገወጥ መንገድ ወደ ሌሎች የአለም ሀገራት የተሰደዱ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ያሉትን ዜጎችም የመመለስ ስራ እየሰራሁ ሲሆን ከሃገር የሚወጡትም ቁጥራቸው ቀላል እንዳልሆነ ሰምተናል፡፡


ከተለያዩ የአረብ ሃገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ያሉ ኢትዮጵያውያንን የመመለስ ስራ መስራት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ ስምንት ሺህ ህፃናትን መቀበሉን የተናገረው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወደ ሀገራቸው ከገቡ በኋላ ግን የትምህርትም አገልግሎት ለማግኘት እንደሚቸገሩ ተመልክቻለሁ ይህ የሆነው ደግሞ ምንም አይነት ማስረጃ ይዘው ስለማይመጡ ነው ብሏል።


በሌላ በኩል ደግሞ ብዛት ያላቸው ተመላሾች ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ወደ ቀያቸው ለመመለስ ስራዎችን እየሰራሁ ቢሆንም ጥቂቶቹ ብቻ በፍቃዳቸው ወደ አካባቢያቸው እንደሚሄዱ ተናግሯል።


በዚህም ተመላሾቹ የመገለል ስሜት ስለሚደርስባቸው እሱን ፍራቻ ወደየአካባቢያቸው አለመመለስን ይመርጣሉ እንደውም መልሰው በህገወጥ መንገድ የሚሄዱ አሉ መባሉን ሰምተናል፡፡


በአለም አቀፍ ደረጃ ከ200 ሚሊየን በላይ ስደተኞች ያሉ ሲሆን ከዚህ ውስጥም ከ180 ሚሊየን በላዩ ለጉልበት ብዝበዛ እንደሚጋለጡ ይነገራል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page