top of page
  • sheger1021fm

ታህሳስ 14፣ 2015- ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ማዕቀፍ አንዲፀድቅ ማድረጓ ተሰማ


ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ማዕቀፍ አንዲፀድቅ ማድረጓ ተሰማ፡፡


ይህን ያደረገችው በቅርቡ በግብፅ ሻርማ ኤል ሼክ ከተማ በተካሄደው የአለም አቀፍ የአየር ለውጥ ጉባኤ ነው፡፡


በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ በብዙሀ ሕይወት ላይ ያጋጠሟትን ችግሮች አቅርባለች ተብሏል፡፡


ኢትዮጵያ በአየር ለውጥ እንደተጎዳች፣ ሀብቶቿ እየተመናመኑ መሆናቸው፣ የአየር ለውጡ መንስኤ ሀገሪቱ እራሷ ሳትሆን ሌሎቹ ሀገራት መሆናቸው፣ ወራሪ መጤ ዝርያዎች የሚያስከትሉት ችግሮችን ጠቅሳለች፡፡


እነዚህን ችግሮች በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትም የሚጋሩዋቸው በመሆኑ የአለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ማዕቀፍ ሊፅድቅ መቻሉ ተነግሩዋል፡፡


በዚህም ምክንያት በማደግ ላይ ላሉ ሀገሮች ለብዙሀ ሕይወት ጥበቃ 200 ቢሊዮን ዶላር በጀት ድጋፍ ፀድቆላቸዋል፡፡


ይህን የሰማነው ከኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መለሰ መሪዮ ነው፡፡

16ኛው የአለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በግብፅ ሻርማ ኤል ሼክ ከተማ በቅርቡ መካሄዱ ይታወቃል፡፡


196 የሚሆኑ ሃገራት የተሳተፉበትና በቻይና ሊቀመንበርነት የተዳረገው ይህ ውይይት፣ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈውበታል፡፡


በአለም አቀፍ ደረጃ በብዝሀ ሕይወት ጉዳት ላይ የተሰራው 23 በመቶ ብቻ መሆኑን የሚጠቅሱት ዶ/ር መለሰ መሪዮ፤ በስምምነቱ ላይ 23 ግቦችን ያቀፈ ማዕቀፍ መሰናዳቱንም ነግረውናል፡፡


ከ23 ግቦች መካከል 8ቱ ለብዝሀ ሕይወት መጥፋት መንስኤ የሆኑ፣ 5ቱ ብዝሀ ሕይወትን በአግባቡ ብንጠቀም ሊያስገኙ የሚችሉ ጥቅሞች መሆናቸውን እና የተቀሩት ደግሞ ማዕቀፉን ለመፈፀም የሚጠቅሙ መሆናቸውም ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡


ቀጣዩን የ2024 17ኛውን የአለም አቀፍ የአየር ለውጥ ጉባኤን የምታሰናዳው ቱርክ መሆኑኗን ሰምተናል፡፡


ብሩክታዊት አስራት


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Recent Posts

See All

የአፍሪካ ህብረት 36ኛው የመሪዎች ጉባኤ የተሳካ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሆቴል ባለቤቶች እና የቱር ኦፕሬተሮች ድርሻ ከፍተኛ ነው ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱኳን አያኖ ተናገሩ፡፡ የኔነህ ሲሳይ ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች በሚገኙ የትራፊክ መብራቶች ላይ የሚደረጉ ልመናዎች እና ህገ-ወጥ ንግዶች ለትራፊክ አደጋ መበርከት ምክንያት ሆነዋል ተባለ፡፡ ይህንንም ለመቆጣጠር ባለሙያዎች ተሰማርተው በአሽከርካሪዎች ላይ ቅጣት እየተጣለ ነው ተብሏል፡፡ ምህረት ስዩም ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

70 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት የድሬዳዋ ወደብና ተርሚናል ዛሬ ተመረቀ፡፡ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት መጠሪያውን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ወደሚል ስያሜ መየቀሩንም ይፋ አድርጓል፡፡ ቴዎድሮስ ወርቁ ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https:

bottom of page