top of page
  • sheger1021fm

ታህሳስ 13፣ 2015- የጋምቢያ መንግስት የተሴረብኝን ወታደራዊ ግልበጣ አከሸፍኩት አለ


የጋምቢያ መንግስት የተሴረብኝን ወታደራዊ ግልበጣ አከሸፍኩት አለ፡፡


የመንግስት ግልበጣ ሞካሪዎቹ በደፈናው ወታደሮቸ ናቸው ከመባሉ ውጭ ዝርዝሩ አልተጠቀሰም፡፡


ስለ ግልበጣው ከገለልተኛ ወገኖች በኩል የተሰማ አስተያየት እንደሌለ ዴይሊ ትረስ ፅፏል፡፡


አራት ወታደሮች ከመንግስት ግልበጣ ሴራው ጋር በተገናኘ ተይዘው መታሰራቸው ተሰምቷል፡፡


የጋምቢያው ፕሬዝዳንት አዳም ባሮው በድጋሚ የተመረጡት ከአመት በፊት ነው፡፡


ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በምዕራብ አፍሪካ አገሮች የመንግስት ግልበጣዎች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡


ጊኒ፣ ማሊ እና ቡርኪናፋሶ የመንግስት ግልበጣ የተደረገባቸው አገሮች ናቸው፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Recent Posts

See All

ባለፉት 11 ወራት ምዕራባዊያን ለዩክሬይን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ሲያስታጥቋት ቆይተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የአሜሪካ እና የጀርመን ስሪት ታንኮችን ታገኛለች መባሉ ከፍተኛ መነጋገሪያ ወጥቶታል፡፡ የኔነህ ከበደ ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page