የሱዳን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር ከ33 ዓመታት በፊት ለተካሄደው ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ አሉ፡፡
ኦማር ሐሰን አልበሽር ለዚያን ጊዜው የመንግስት ግልበጣ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ያሉት በካርቱም ጉዳያቸውን ለሚያየው ፍርድ ቤት እንደሆነ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡
አልበሽር ከዚያን ጊዜ አንስቶ አገሪቱን ለ30 ዓመታት ያህል መርተዋታል፡፡
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ለግልበጣው ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ቢሉም ምንም ዓይነት መፀፀት አልተስተዋለባቸውም ተብሏል፡፡
አልበሽር በስልጣን በቆዩባቸው ዓመታት የአገሪቱን ብሔራዊ መግባባት በማስፈን የነዳጅ ዘይት በማልማት እና የመሰረተ ልማት በማስፋፋት ታላቅ ተግባር እንዳከናወኑ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
መንግስት በገለበጡበት ወቅት ሲቪሎች እንዳልተካፈሉ ለፍርድ ቤቱ አረጋግጠዋል ተብሏል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments