በአሜሪካ ሰሜናዊ ካሊፎርኒያን ያናወጠ ርዕደ መሬት ሁለት ሰዎችን ገደለ፡፡
የመሬት ነውጡ በርዕደ መሬት መለኪያ (ሬክተር ስኬል) 6.4 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ርዕደ መሬቱ ብዙ መንገዶችን ከጥቅም ውጭ ማድረጉን ABC ኒውስ ፅፏል፡፡
በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶችንም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማቋረጡ ታውቋል፡፡
የመሬት ነውጡ ተጨማሪ ንቅናቄዎችን መፍጠሩ ስለማይቀር የአካባቢው ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተመክረዋል ተብሏል፡፡
የኔነህ ከበደ
ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Comments