ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል የጀመረው ህንፃ ለመጨረስ 1.5 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ተናገረ፡፡
ማዕከሉ እየተገነባ ያለው ባለ ስድስት ወለል ህንፃ ሙሉ ለሙሉ በስሩ እየተረዱ ላሉ ሴቶች ሲሆን ወደፊት ተጨማሪ 2 ባለስድስት ወለል ህንፃ ለወንዶች ማረፊያ እና የእደ ጥበብ ማስተማሪያ ማገገሚያ እና መዝናኛ ማዕከል የያዘ ህንፃ ለመገንባት አቅዷል ተብሏል፡፡
የማዕከሉ መስራች ሊቀህሩያን መለሰ አየለ ግንባታው የተጀመረው ህንፃ ስራ እስካሁን ሲካሄድ የነበረው በራሱ በማዕከሉ አቅም የነበረ ሲሆን ለዚህም 50 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጓል ብለዋል፡፡
ህንፃውን ለማጠናቀቅ የህብረተሰቡ ትብብር ከሌለ ግንባታውን መፈፀም አይቻለንም ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለዚህ ትብብር ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የህንፃው አሰሪ ኮሚቴ አስተባባሪ ኢንጅነር አቤል ተፈራ ‘’አሁን የሚገነባው ባለ ስድስት ወለል ህንፃ በ502 ካሬ ላይ አርፏል’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ግንባታው ሲጠናቀቅ ታማሚዎች እና ነርሶችን ጨምሮ እስከ 5,000 ሰው ይይዛል፡፡
‘’ #ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል በአጠቃላይ በ3 ምዕራፍ ግንባታዎች ለማካሄድ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው’’ ያሉ ሲሆን ‘’ይህ የመጀመሪያው ዙር ግንባታ እንዲጠናቀቅ እገዛን ይሻል’’ ብለዋል፡፡
የማዕከሉ አምባሳደር ተዋናይ ዳዊት አባተ ‘’ለሴቶቹ ተከራይቶት የነበረው ማረፊያ የቤት ኪራይ መክለፍ ስላቃተው አሁን ወዳለው ስፍራ ለማዘዋወር ተገዷል’’ ብሏል፡፡
አሁን ያሉበት ማረፊያ ደግሞ በዘላቂነት አያገለግልም ተብሏል፡፡
ማዕከሉ ባለፉት 20 ዓመታት 1,500 የሚሆኑ የአዕምሮ ህሙማንን ተቀብሎ የረዳ ሲሆን 450 የሚሆኑት አገግመው ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments