top of page

ታህሳስ 11፣2017 - የጋምቤላ ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ ተሰረዘ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጋምቤላ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄን (ጋ.ብ.ዲ.ን) ከፓርቲነት መሰረዙን ባወጣው ደብዳቤ እወቁት ብሏል፡፡

 

ፓርቲው በ2016 ዓ.ም ከቦርዱ የሚሰጠውን ድጋፍ ለማግኘት #የሴትና የአካል ጉዳተኛ አባላቱን ቁጥር በቃለ መሃላ አስደግፎ በማቅረብ ገንዘብ መውሰዱን ቦርዱ አሳታውሷል፡፡

 

ምርጫ ቦርድ ፓርቲው በወቅቱ ያቀረበው የሴትና የአካል ጉዳተኛ አባላቱ ቁጥር አላሳመነኝም የተጋነነ ነው በማለት ሌሎች ፓርቲዎችን እንደጠየቀው ሁሉ ጋ.ብ.ዲ.ንን ለትክክለኛነቱ ማስረጃ  ይቅረብልኝ ሲል ይጠይቃል፡፡

በጋምቤላ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በኩል በድጋሚ የቀረበው የሴትና #የአካል_ጉዳተኛ አባላቱ ቁጥር አስቀድሞ ካቀረበው ቁጥር እጅግ ዝቅ ያለ መሆኑን ቦርዱ ተናግሯል፡፡

 

ይህንንም አሃዝ የሚደግፍ ማስረጃ እንዲያቀርብ የተጠየቀ ቢሆንም ማቅረብ አልቻለም ያለው ቦርዱ

ፓርቲው ታግዶ በእነዚህ አባላቱ ቁጥር ልክ የወሰደውን ገንዘብ እንዲመልስና ልሰረዝ አይገባም የሚልበትን ምክንያት እንዲያቀርብ የተጠየቀ ቢሆንም እስካሁን ምክንያት ማቅረብ እንዳቻለና ገንዘቡንም እንዳልመለሰ ጠቅሷል፡፡

 

በመሆኑም ቦርዱ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ፓርቲውን መሰረዙንና አመራሮቹም በጋምቤላ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ስም እንዳይንቀሳቀሱ ወስኗል፡፡

 

ፓርቲው በ2016 ዓ.ም የተጋነነ ነው በተባለው የሴትና የአካል ጉዳተኛ አባላቱ ቁጥር የወሰደውን 270,883 ብር በህግ ተከስሶ እንዲመልስ መወሰኑን ቦርዱ ባወጣው ደብዳቤ እወቁልኝ ብሏል፡፡

 

ምንታምር ፀጋው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

 

 

Comments


bottom of page