ባሳለፍነው ሳምንት ኢትዮጵያን እና ሌሎች የአለም ክፍሎችን ያዳረሰው የሳይቤሪያ ቅዝቃዜ ከትናንት ጀምሮ እየቀነሰ እንደሆነ የብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡
የኢንስቲትዩቱ የሜትዮሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) ሌሊትና ንጋት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ይስተዋል የነበረው ከሳይቤሪያ ተነስቶ ኢትዮጵያንና ሌሎች የአለም ክፍሎችን ያዳረሰው #ቅዝቃዜ እየቀነሰ መሆኑን ነግረውናል፡፡
በሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ትግራይ፣ በምስራቅ አማራ፣ በመካከለኛው ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በሰሜን ሸዋ ፍቼ እንዲሁም ሐረርና ጅግጅጋ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ተስተናግዷል ብለዋል፡፡
‘’ከታህሳስ 9/2017 ጀምሮ እየቀነሰ የመጣው ቅዝቃዜ በመጪዎቹ 10 ቀናት ጨርሶ እየጠፋ ይሄዳል’’ ብለዋል ዶ/ር አሳምነው፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ወንድሙ ሀይሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments