ቴክኖ ሞባይል በቅርቡ ለዓለም ያስተዋወቀው የቴክኖ ኤአይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በአዲስ አበባ አስተዋወቀ፡፡
አዲሱ የቴክኖ ኤአይ ( Tecno AI ) አጋዥ ቴክ ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ የተለያዩ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየር እና መሰል ተያያዥ ስራዎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመስራት የሚያስችል አጋዥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ተካቶለታል ተብሏል፡፡
የቴክኖ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሊክ "ቴክኖ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ጉልህ ሚናን እየተጫወተ እንደሚገኝ" ጠቅሰዋል።

አቶ አሊክ "ቴክኖ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን እንዲሁም ማህበረሰቡ አለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ እኩል እንዲራመድ መትጋቱን እንደሚቀጥል" አረጋግጠዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ ስለ የፋንተም V2 የታጣፊ ስልኮች ከቴክኖ ኤአይ ጋር አጣምረው ስለመጡት ቴክኖሎጂ በምስል የታገዘ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በዝግጅቱ ላይ ከኤአይ ቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ እንደ VR ያሉ የኤይአይ ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጌሞች ላይ የዝግጅቱ ታዳሚዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በተጨማሪም የስልኮቹን የካሜራ ብቃት የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን ለዕይታ ቀርቧል፡፡
ቴክኖ ሞባይል ከአለም የቴክኖሎጂ ገበያ ጋር ተወዳዳሪ የሆኑ እና ከፍ ያለ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ወደ ተጠቃሚ ማድረሱን ቀጥያለሁ ብሏል።
ቴክኖ ሞባይል በአዲስ አበባ ከተማ ጎሮ አይሲቲ ፓርክ ባስገነባው ዘመናዊ ፋብሪካ የሚገጥማቸውን ዘመናዊ የሞባይል ስልኮች ለተለያዩ ሀገራት እየላከ ዶላር እያስገኘ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments