የበዓላት መዳረሻ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ የሚፈጠረውን የምርት እጥረት እና የሸቀጦች የዋጋ መናር እንዳይኖር ከዚህ ቀደም እንደማደርገው ባዛሮችን አሰናድቼ እየጠበቅኳችሁ ነው ሲል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ተናገረ፡፡
ለመጪው ገና በዓልም #አምራቾች ወደ ከተማዋ መጥተው ከሸማቹ ጋር በቀጥታ የሚገናኙበትን መንገድ አመቻችቻለሁ ብሏል፡፡
በዚህም መውጫ በሮች ላይ የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጃቸው 4ቱም የገበያ ማዕከላት (ኮልፌ፣ አቃቂ፣ ለሚ ኩራ እና ላፍቶ) ምርቶችን በብዛትም በቅናሽም ታገኛላችሁ ያሉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ፍስሐ ጥበቡ ከላፍቶ የገበያ ማዕከል በስተቀር በሌሎቹ የገበያ ማዕከላት የአትክልት እና የሰብል ምርት እየቀረበ ነው ብለዋል፡፡
ሸማቾች ላፍቶ #የገበያ_ማዕከል ብትሄዱ ደግሞ አትክልት እና የፍራፍሬ ምርቶችን ነው የምታገኙት ሲሉ ምክትል ሀላፊው ተናግሯል፡፡
የቅዳሜ እና እሁድ ገበያም 3 ዓመት ያለፈው መሆኑን የተናገሩት አቶ ፍስሀ 197 የሚሆኑ ማዕከላት ስላሉ እዚያ በመሄድ መሸመት ትችላላችሁ ብለዋል፡፡
የገና በዓል መዳረሻ ወቅት ላይ ቀናቶች ሲቀሩት በ14 ቦታዎች ባዛሮችን አዘጋጃለሁ ያለው ቢሮው በባዛሩም አምራቾች፣ ኢንዱስትሪዎች እና አርሶ አደሮች ምርታቸው ቀጥታ አምጥተው ከሸማቹ ጋር የሚገናኙበትን መንገድ ዘርግቻለሁ ብሏል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
コメント