top of page

ታህሳስ 11፣2017 - በቀደሙት ጊዜአት የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት ክፍተት እንዳለበት ሲነገር ቆይቷል፡፡

  • sheger1021fm
  • Dec 20, 2024
  • 1 min read

በቀደሙት ጊዜአት የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት ክፍተት እንዳለበት ሲነገር ቆይቷል፡፡


ከዚህ ቀደም ዘርፉ እያስተናገደ ነው የሚባለውን ችግር ይፈታል የተባለ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ተቀርፆ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡


በ2015 ዓ.ም ቅድመ አንደኛ ተማሪዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ ሲገባ 1ኛ እና 2ተኛ ደረጃ ላይ ደግሞ በሙከራ ደረጃ ሲተገበር እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡


ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ ገብቶ የመማር ማስተማሩ ቀጥሎ ቆይቷል፡፡


ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው አዲሱ #ሥርዓተ_ትምህርት ከቀደመው ሥርዓተ ትምህርት ቀየር ያደረጋቸው ለውጦች አሉ፡፡


ከእነዛም መካከል የ7ተኛ እና 8ተኛ ክፍል Biology, Chemistry እና Physics ከዚህ ቀደም በተናጥል ሲሰጡ የነበሩ የትምህርት ዓይነቶች በአንድ ተደርገዋል፡፡


በተጨማሪም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ብቻ እንዲማሩ መደረጉ እና ግብረ ገብ የተሰኘ የትምህርት ዓይነት በትምህርት ሥርዓቱ መካተቱ ከለውጦቹ መካከል ናቸው፡፡


በዚህ ሂደት ውስጥም ሸገር ራዲዮ በተለያዩ ጊዜያት ያነጋገራቸው የትምህርት ባለሙያዎች አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በተወሰነ መልኩ ሊስተካል ይገባል፤ የሚወጣው ወጥቶ መካተት የሚያስፈልገው መካተት አለበት ሲሉ ይደመጣል፡፡


ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው ይሄው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ምን ዓይነት በጎ ጎን አለው? ሂደቱስ ምን ይመስላል?


በታሰበው ልክ መሻሻሎች ይመጣሉ ተብሎ ተስፋ ይጣልበታለው ወይ የሚሉ እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን ለሰላሳ ዓመታት በትምህርት ዘርፉ ላይ የቆዩትን አቶ ተስፋዬ ለጋን ጠይቀናቸዋል፡፡



ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Recent Posts

See All
የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡

ጥር 12/2018 የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር "ስራቸውን በአግባቡ አልሰሩም፣ ህግን አላከበሩም ፣ ኦዲት ሪፖርት ለዓመታት አላቀረቡም ፣ጠቅላላ ጉባዔም ወቅቱን ጠብቀው ማካሄድ አልቻሉም"በሚል ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡ የቀድሞ ቦርድ አባላት ስራቸወን በአግባቡ ባለመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page