የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ትምህርት በተገቢው ልክ አላስተማረም በሚል እና በሌሎች ምክንያቶች የቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤቶችን ፍቃድ መሰረዙን ተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት ተናገረ፡፡
ትምህርት ቤቱ በበኩሉ አፋን ኦሮሞ በአዲስ አበባ ባሉ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ ከተማ አስተዳደሩ መመሪያ ያወጣው ዘንድሮ መሆኑን በመጥቀስ እኔ ግን ከአምና ጀምሮ ትምህርት እየሰጠሁ ነው፤ የሚቀርብብኝ ክስም ሃሰት ነው ብሏል፡፡
ለምን ትምህርት ቤቱን መዝጋት እንደተፈለገም አልገባኝም ሲል ለሸገር ተናግሯል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Kommentare