በኢትዮጵያ በክልል ዋና ዋና ከተሞች ላይ በተደረገ ጥናት በአንድ ከተማ ላይ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለመሆን 30 በመቶቹ የመክፈል አቅም የላቸውም ተባለ፡፡
ኢትዮጵያ ለዜጎቿ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የንጽህና አጠባበቅ ላይ የተለያዩ ስራዎች ከውና ውጤት ያመጡ ቢኖሩም አሁንም ግን ዘርፉ ክፍተቶች አሉበት ተብሏል።
የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲሁም የሳኒቴሽን አገልግሎቱን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ በ USAID የሚደገፍና #URBAN_WASH የተባለ ፕሮጀክት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተለያዩ ድጋፎች እያደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በፕሮጀክቱ አውደ ጥናት ላይ ተገኝተን እንደሰማነው የከተሞች በተለይም በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሰራው URBAN WASH በከተሞች ያለውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት የተመለከቱ የተለያዩ ጥናቶች ሲከውን ነበር ተብሏል፡፡
በ #USAID URBAN WASH ፕሮጀክት አማካሪ የሆኑትን አቶ ዮሴፍ ከበደ የውሃ ሳንቲሽን አገልግሎትን ተደራሽነት ማስፋፋት ነው በተለይ ደግሞ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች እነዚህን አገልግሎቶች እንዲያገኙ፤ የመጠጥ ዉሃ መሰረተ ልማቶች ግንባታ የሳኒቴሽን መሰረት ልማት ግንባታ ይከወናል ብለዋል፡፡
#የንጹህ_መጠጥ_ውሃ አቅርቦት አለመሟላት ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ላላቸው የከተማ ነዋሪዎች ተጨማሪ ወጪ የሚያስከትልና ባለው ችግር ላይ ጫና የሚፈጥር እንደሆነም አቶ ዮሴፍ ተናግረዋል፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ቅርቦት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይማኖት በለጠ በበኩላቸው መንግስት የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት ለማቅረብ በራሱ ከሚከውናቸው ስራዎች በተጨማሪ ከአጋር አካላት ጋር የሚሰሩ ፕሮጀክቶች በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል፡፡
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments