top of page

ታህሳስ 10፣2016 - የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ ያሉ የስራ ሀላፊዎቼና ሰራተኞቼ በየቦታው ተንቀሳቅሰው እንዳይሰሩ ስጋት አለኝ አለ፡

ባንኩ በፕሬዘዳንቱ በኩል በኢትዮጵያ ላሉ ሰራኞቹና አባሎቹ በሙሉ ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባቸው የነሱን ደህንነት ማስጠበቅ ሀላፊነቱ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡


የአፍሪካ ልማት ባንክ ከወር ከ15 ቀን በፊት በአዲስ አበባ ከፍተኛ የስራ ሀላፊው ላይ ጥቃት እንደደረሰበት በመግለጫው አስታውሷል፡፡


ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳዩ ምርመራና ማብራሪያ ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡


ሆኖም የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዘዳንት በዚህ ጉዳይ ኢትዮጵያ በምርመራውና ተያያዥ ጥቃት ጉዳይ ያለችው ነገር የለም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን በኢትዮጵያ ቢሮውን ሙሉ ለሙሉ ሳይዘጋ ለሰራተኞቹ ደህንነት ሲባል ሰራተኞቹን ከአዲስ አበባ እንደሚያነሳ በመግለጫው ተናግሯል፡፡


የአፍሪካ ልማት ባንክ በአዲስ አበባ ያለውን ቢሮ ሳይዘጋ በአንድ ተወካይ ኦፊሰር ክፍት እንደሚያደርግ ተነጋግሮ ጠቅላላ የውጭ ሰራተኞቹን ግን ከአዲስ አበባ እንደሚያወጣ ወስኗል፡፡


ከዚህ ቀደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም የተፈጠረው ነገር ባንኩ በኢትዮጵያ ያለውን ቢሮ የሚያዘጋው እንደማይሆንና ከኢትዮጵያ ጋር ያለውም ግንኙነት እንዲያቋርጥ አያደርገውም ማለታቸው ይታወሳል፡፡



ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page