top of page

ታህሳስ 10፣2016 -የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳልፏል

የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሣ የሚከፈልበትን እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የቀረበው ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ አንዱ ነው፡፡


ካሣን የመተመን፣ የመክፈልና ተነሺዎችን መልሶ የማቋቋም ኃላፊነት የተጣለባቸውን አካላትና ግዴታዎቻቸውን ግልጽ ማድረግ በማስፈለጉ ማሻሻያው መዘጋጀቱ ተነግሯል።


የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅም በምክር ቤቱ ውይይት ተደርጎበታል።


የሕዝብ በዓላትን፣ የዕረፍት ቀናትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ እንዲሁ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውይይት አካሂዷል።


በሶስቱ ረቂቅ አዋጆች ላይ ምክር ቤቱ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።


የአምራች ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ ደግሞ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ነው የወሰነው።


መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page