top of page

ታህሳስ 1፣2016 የምግብ እጦት እና የስርዓተ ምግብ ችግር ለመፍታት የዘርፉ መሪዎችን አቅም እያበረታሁ ነው ሲል የአፍሪካ የግብርናመሪዎች ማዕከል ተናገረ

 አፍሪካ ያልፈታችውን፣ አንዳንዴም ወደኋላ የሚመለስባትን የምግብ እጦት እና የስርዓተ ምግብ ችግር ለመፍታት የግብርና ተመራማሪዎችን፣ የዘርፉን መሪዎችን አቅም እያበረታሁ ነው ሲል የአፍሪካ የግብርና መሪዎች ማዕከል ተናገረ፡፡

 

ማዕከሉ የአፍሪካ ሀገራት የግብርናው ዘርፍ ለመለወጥ የሚያወጧቸውን ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ወደ መሬት ለማውረድ ብርቱ ሀላፊነት ያለባቸውን መሪዎችም እያሰለጠንኩ ነው ብሏል፡፡

 

ሰሞኑም በዚሁ ማዕከል አማካይነት 1 ዓመት ከ6 ወር ያህል ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 76 የግብርና መሪዎች ስልጠናቸውን አጠናቀው በአዲስ አበባ ተመርቀዋል፡፡

 

ስልጠናውን ሲከታተሉ የነበሩት የግብርና ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ፣ ከጋና፣ በኬንያ፣ ከማላዊ፣ ከናይጀሪያ፣ ከሩዋንዳ፣ ከታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የተወጣጡ መሆናቸውን ማዕከሉ አስረድቷል፡፡

 

ከዚህ የመካከለኛ የግብርና ዘርፍ ሀላፊዎች ስልጠና ላይ ለመሳተፍ ከ100 በላይ አመልካቾች አመልክተው እንደነበር ሰምተናል፡፡


እድሉን አግኝተው ስልጠናቸው ወስደው ከጨረሱት 76 መሪዎች መካከል 45 በመቶዎቹ ከስምንት ሀገራት የመንግስት ተቋማት፣ 26 በመቶዎቹ ደግሞ ከግሉ ዘርፍ እና 29 በመቶዎች ከሲቪል ማህበራት መሆናቸወ ተነግሯል፡፡

 

የኢትዮጰያ የግብርና ዘርፍ ሀላፊዎችን ጨምሮ ከስምንቱ ሀገራት ተወጣተው ስልጠናውን የወሰዱት 76 ሰዎች የሀገሪቱን የግብርና ስርዓት እንዲሻሻል ፣ እንዲለወጥ የማድረግ ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡

 

የአሁኖቹ ሰልጣኞች ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች ሲሆኑ ከዚህ ቀደም 80 ሰዎች ስልጠናውን መውሰዳቸውን ሲነገር ሰምተናል፡፡

 

የአፍሪካ የግብርና መሪዎች ማዕከል /CALA/ ፕግራሙን የነደፈው የአህጉሪቱን የግብርና ሥርዓት ለማሻሻል ከሚሰራው አግራ ድርጅት ጋር በመተባበር መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

 

 

ንጋቱ ሙሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

留言


bottom of page