በአዲስ አበባ በሚሰራው የኮሪደር ልማት ደንብ ተላልፈዋል ከተባሉ ተቋማት እና ግለሰቦች በ5 ወር ውስጥ ከ103 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል ተባለ፡፡
ይህንን ያለው ከአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ነው፡፡
በከተማዋ ተሰርተው አገልግሎት መስጠት የጀመሩ፣ አሁንም በስራ ላይ ያሉ #የኮሪደር_ልማት ፕሮጀክቶች ረዘም ላለ ጊዜ እንከን ሳይገጥማቸው እንዲያገለግሉ ለማድረግ የቁጥጥር ስራዎች እየተከወኑ ነው ብሏል መስሪያ ቤቱ፡፡
በዚህም ከግለሰብ እስከ ድርጅት የኮሪደር ልማቱ ላይ ደንብ ተላልፈው የተገኙትን ለመቅጣት እና ግንዛቤ ለመፍጠር በ2017 በጀት ዓመት 5 የመንግስት ተቋማት በጋራ መስራት መጀመራቸውንም ሰምተናል፡፡
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ የግንባታ ፈቃድና እና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እና የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን አብረው ለመስራት የተስማሙ ተቋማት ናቸው፡፡
ተቋሞቹም በ5 ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን ለመመልከት ሲገጥሟቸው ስለነበሩ ችግሮች እና ወደፊት ሊሰሩት ስላቀዷቸው ተግባራት መክረዋል፡፡
ከደንብ ተላላፊዎች ተገኝቷል የተባለው ይህ #ቅጣት ከመንግስታዊ ተቋማት ጭምር የተሰበሰበ መሆኑን የሚናገሩት የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አምስቱም ተቋማት በየዘርፋቸው ደንብ ተላልፈዋል ካሏቸው አካላት የተሰበሰበን የገንዘብ መጠን የመንግስት ካዝና ውስጥ አስገብተዋል ብለዋል፡፡
የኮሪደር ልማቱ አገልግሎት መስጠት ከጀመረት ጊዜ አንስቶ በምናደርገው ቁጥጥር ላይ ችግሮች ሲገጥሙን ነበር ያሉት ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አሽከርካሪዎች በ #መሰረተ_ልማቶች ላይ ማለትም ዘንባባዎችን እና ፖሎችን መግጨታቸው አንዱ ችግር እንደነበረ ተናግረዋል፡፡
የተሰሩትን መሰረተ ልማቶች በአግባቡ አለመጠቀምም ሌላኛው በቁጥጥር ስራው ሲገጥሙን ከነበሩ ተግዳሮቶች መካከል ናቸው ብለዋል፡፡
የኮሪደር ልማቱን ደንብ የሚተላለፉ እና ቅጣት የሚጣልባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሱ ነው ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios