top of page

ታህሣስ 3፣2017 - ''በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የስራ ኃላፊዎች ላይ የሚፈፀም ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሊቆም ይገባል''

የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፣ በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የስራ ኃላፊዎች ላይ የሚፈፀም ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሊቆም ይገባል ብሏል፡፡

 

ማዕከሉ በግጭት ውስጥ ላለ ሀገር በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን መደገፍ እንጂ ጫና ማሳደር፣ ዛቻ እና ማስፈራራት ተገቢ አይደለም ብሏል፡፡

 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ በሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ተቋማት ላይ ይፈፀማል ስለተባለው ዛቻ ማስፈራሪያ እና ማዋከብ ‘’ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር እየተነጋገርኩ ነው’’ ሲል ተናግሯል፡፡

 

የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዱ ተግባራትን አከናውነዋል በሚል ምክንያት ከሳምታት በፊት ሶስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መታገዳቸው ይታወሳል፡፡

 

የታገዱት ድርጅቶችም የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል፣ ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች የተሰኙ ድርጅቶች ናቸው፡፡


ያሬድ እንዳሻው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

 

 

Comments


bottom of page