top of page

ታህሣስ 2፣2017 - ‘’ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸዉ ዓይነ ስውራን የራሳቸው ምስክርነት እንደ ምስክርነት ባለመቆጠሩ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል’’

  • sheger1021fm
  • Dec 11, 2024
  • 1 min read

‘’ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸዉ ዓይነ ስውራን የራሳቸው ምስክርነት እንደ ምስክርነት ባለመቆጠሩ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል’’ ሲል የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማህበር ተናገረ።


ማህበሩ በአካል ጉዳተኛ ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጾታዊ ጥቃት በዓይነቱም በብዛትም እየጨመረ ነው ብሏል።


የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ድባቤ ባጫ እንደ ማህበር ‘’ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸውን አካል ጉዳተኞች ፍትህ እንዲያገኙ እገዛ እያደረግን ነው ሆኖም ግን በተለይ ዓይነ ስውራን ሴቶች ጾታዊ ጥቃት ሲደርስባቸው ጥቃት ያደረሰባቸውን አካል በድምፅ በመለየት ምስክርነት እንዲሰጡ የሚያደርግ አሰራር ባለመኖሩ ፍትህ ለማግኘት ይቸገራሉ’’ ሲሉ ነግረውናል።


በሴት አካል ጉዳተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጾታዊ ጥቃት እንዲጨምር ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ ድህነት እና የግጭቶች መስፋፋት ተጠቃሽ መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ወ/ሮ ድባቤ ይናገራሉ።


በተደራራቢ ችግር ውስጥ ያሉ ወጣቶች ላይ የሚሰራው የአይፓስ (Ipas) ኢትዮጵያ የሜክ ዋይ (Make way) ፕሮግራም አማካሪ በፀሎት መንገሻ በበኩላቸው በተለይ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ከሚደርስባቸው ጾታዊ ጥቃት ባሻገር የሥነ ልቦና ጥቃትም እንደሚደርስባቸው ነግረውናል።


በአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ የሆኑት ራሔል አንበርብር የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞች መብት እንዲከበር የህግ ክፍተት ሳይሆን የአፈጻጸም ችግር ነው ያለበት ብለዋል።


አያይዘውም ጥቃት የደረሰባትን አካል ጉዳተኛ ፍትህ እንድታገኝ የምርመራ አካሄዱ የዘመነ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡


ፍትህ አካላት ላይ ከፍተኛ የአፈፃፀም ችግር አለ ያሉት አቃቢ ህግ ራሔል የምርመራ የክህሎት ችግር መኖርም ፍትህ እንዳይሰፍን እክል መሆኑንም ተናግረዋል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page