top of page

ታህሣስ 2፣2017 - የኢትዮጵያ የታክስ ህጎች የውጭ ኢንቨስተሮች በቀላሉ በቋንቋቸው እንዲያገኙት ሆኖ ተሰናድቷል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ የታክስ ህጎች የውጭ ኢንቨስተሮች በቀላሉ በቋንቋቸው እንዲያገኙት ሆኖ ተሰናድቷል ተባለ፡፡


ስለ ጉዳዩ የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡


ኢትዮጵያ የፃፈችው ያረቀቀችው የታክስ ህግ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ እንዲረዳው የውጭ ኢንቨስተሮችና አለም አቀፍ የልማት አጋሮች ማግኘት እንዲችሉ ጭምር በድረ ገፅ ሰፍሯል ተብሏል፡፡


ይህ ከ100 በላይ በአማርኛ ብቻ የተፃፈው ህግ ወደ እንግሊዘኛ ተተርጉሞ ሌሎችም 300 ግድም የሚሆኑ የታክስ ህጎች በአመቺ መንገድ ለውጭ ማህበረሰብ ቀርቧል ተብሏል፡፡


የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እየተጓዘች በመሆኑ ህጎቹን ለውጪ ኢንቨስተሮች ጭምር ተደራሽ ማድረጉ ለስራው ያግዛል ብለዋል፡፡


ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ማዕዘንም በኢትዮጵያ ከፍ ያለ ንግድ ከፍ ያለ አለም አቀፍ ኢንቨስትመንት እንዲመጣ እየሰራን ለመሆኑ ይህ የታክስ ህግ በቀላል መንገድ መስፈሩ ከፍ ያለ ቦታ እንደሚሰጠው የገንዘብ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page