ታህሣስ 2፣2017 - ''የአውሮፕላን ማረፊያው፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ይጠናቀቃል''
- sheger1021fm
- Dec 11, 2024
- 1 min read
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያ ይሆናል የተባለ፤ የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት የቦታ ርክክብ ተደረገ፡፡
መለስተኛ አውሮፕላኖችን እንዲያስተናግድ ታሳቢ ተደርጎ ይገነባል የተባለው ይህ #የአውሮፕላን_ማረፊያ፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ይጠናቀቃልም ተብሏል፡፡
የአውሮፕላን ማረፊያው የሚገነባው በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ መሆኑ ተነግሯል፡
ግንባታው የሚከወነው በአቢሲኒያ ፍላይት እና በቲናው አበባ ልማት አክሲዮን ማህበር አማካኝነት እንደሆነ ሰምተናል፡፡

አሁን ርክክብ የተደረገው ቦታ ስፋት 6 ሄክታር መሆኑንና እንደየአስፈላጊነቱ ሊሰፋም ይችላል ተብሏል፡፡
‘’የአውሮፕላን ማረፊያው መገንባት የጥቅሙ ብዙ ነው’’ ሲሉ የቲናው አበባ ልማት አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ ተስፋዬ ገብረኸት ነግረውናል፡፡
በተለይም ‘’በአካባቢው ኢንቨስት ለማድረግ የሚፈለጉ ባለሀብቶችን የሚስብ ነው’’ ብለዋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አንድም የአውሮፕላን ማረፊያ እንደለሌ ያስታወሱት በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ አስተዳዳሪ ዘውዱ ዱላ ‘’የአውሮፕላን ማረፊያው ሲጠናቀቅ ለ #ጉራጌ_ዞን ብቻ ሳይሆን ለአጎራባች አካቢዎችም የሚጠቅም’’ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተለይም አካባቢው አንጻራዊ ሰላም ያለበት በመሆኑ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ቱሪስቶች ሊመላለሱበት የሚችሉበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ይገነባል የተባለው መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያ ወደፊት ይበልጥ ሰፍቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ተረክቦት የትልልቅ አውሮፕላኖች ማረፊያ የመሆን እድል ያለው ነው ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments