top of page

ታህሣስ 2፣2017 - የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የአቅርቦት ሰንሰለቱን ዘመናዊ ለማድረግ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመስራት መምከሩ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Dec 11, 2024
  • 2 min read

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የአቅርቦት ሰንሰለቱን ዘመናዊ ለማድረግ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከሩ ተነገረ፡፡


የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በሀገሪቱ ብቸኛ የመንግስት የህክምና ግብዓቶችን የሚገዛ ፣ የሚያከማችና የሚያሰራጭ ተቋም በመሆኑ የአቅርቦት ሰንሰለቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በርካታ ስራዎችን እየከወነ መሆኑን ተናግሯል፡፡


ተቋሙ የመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓቱን ቴክኖሎጂ በማዘመን ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተናግሯል፡፡


ዘመናዊ የመድኃኒት የቆጠራ ሥርዓት፣ የሥርጭት አስተዳደር፣ ዘመናዊ የሲስተም መቆጣጠሪያ ሥርዓት፣ CCTV (የቅኝት ካሜራዎችን መትከል)፣ ዘመናዊ የመጋዘን አስተዳደር ሥርዓት አተገባበር እና ሌሎችም የአገልግሎቱን የመድኃኒት አቅርቦት ዘመናዊ ሊያደርጉ የሚችሉ የቴክኖሎጂ ስራዎች በኢትዮ ቴሌኮም የሚከወኑ ናቸው ተብሏል፡፡


የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማዘመን በርካታ የቴክኖሎጂ ስራዎችን ማስጀመሩን እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮ ቴሌኮም ከቀረቡት የቴክኖሎጂ አማራጮች መካከል የተሽከርካሪዎችን በግብአት ሥርጭት ወቅት ያሉበትን ሁኔታ የሚያመላክት መቆጣጠሪያ "GPS "ስርዓት እንዲሁም የ "Bar Coding" "የQR code" ስራ ላይ ማዋል ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እንዲሁም የድሮን ቴክኖሎጂ መተግበር ይገኙበታል፡፡


በተጨማሪም የተቋሙን የደንበኞች ነጻ የጥሪ ማዕከልን ማዘመን፣ዘመናዊ የስራ አካባቢን መፍጠር፣ የአገልግሎቱን ማስተር ዳታ ማከማቻ እንዲኖር ማገዝ፣ ዘመናዊ የመጋዘን እና የኢንቬንቶሪ አስተዳደር፣ የመግቢያ እና መውጫ በሮች ማዘመን የሚሉት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ የሚሰራባቸው ናቸው ተብሏል፡፡


ሌሎች ትኩረት መደረግ ያለባቸውና ለመድሃኒትና የህክምና ግብዓት አቅርቦት ሰንሰለቱ ጠቃሚ የሆኑ፣ ስራን የሚያቃልሉና የሚያቀላጥፉ ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማካተት በጋራ ለመስራት ከኢትዮ_ቴሌኮም ቡድን ጋር ምክክር ተደርጓል።


በስራ ላይ የሚውሉት የአሰራር ሥርዓቶች አገልግሎቱ እየተገበረ ካለው የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት (ERP) የሚናበቡ እና ያሉትን 19 ቅርጫፎች ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን አካባቢዎችን ከፍተኛ የትኩረት ቦታዎች ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡


የኢትዮ ቴሌኮም ቴክኒካል ቡድን ከአገልግሎቱ የተመረጡ የቴክኒክ ቡድን ጋር በመተባበር ስራ ላይ በሚውሉ ቴክኖሎጂዎች ላይ አገልግሎቱ ያለበትን ሁኔታ በማየት፣ በሂደት ላይ ያሉትን ስራዎችን በመለየት፣ ሁለቱ ተቋማት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመው ሙሉ በሙሉ ስራው ወደ ትግበራ ይገባል መባሉን ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ሰምተናል፡፡


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page