top of page

ታህሣስ 2፣2017 - ‘’አካል ጉዳተኞችን ለማገዝ በሚል ተመስርተው የለግል ጥቅም የሚሰሩ ማህበራት አሉ’’ የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር

  • sheger1021fm
  • Dec 11, 2024
  • 1 min read

‘’አካል ጉዳተኞችን ለማገዝ በሚል ተመስርተው የለግል ጥቅም የሚሰሩ ማህበራት አሉ’’ ሲል የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር ተናገረ፡፡


የተለያዩ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎችን ለመደገፍ የተመሰረቱና መልካም የሚባል ስራ የሚሰሩ ማህበራት ቢኖሩም በአካል ጉዳተኞች ስም ተመስረተው #የግለሰቦች_ጥቅም ማግኛ የሆኑ ማህበራት እንዳሉ ተነግሯል፡፡


የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዝደንት ወይንሸት ግርማ(ዶ/ር) ‘’በአካል ጉዳተኞች ስም ድርጅት አቋቁመው እንደ ንግድ የሚሰሩ አሉ’’ ብለዋል፡፡

በእንዲህ አይነት ተግባራት የተሰማሩ ማህበራትን ለማጥራት የኦዲት ፍተሻ ሊደረግቸው ይገባል ያሉ ሲሆን ይህም የመንግስት ሀላፊነት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡


በአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን ግንዛቤ ስርጸትና የማህበረሰብ ንቅናቄ ቡድን መሪ አየሁ ደመቀ ‘’ #አካል_ጉዳተኞችን መሰረት አድርገው የተቀቋቋሙ የተለያዩ ማህበራት አሉ፣ አውንታዊ አስተዋፅኦአቸውም ብዙ ነው’’ ብለውናል፡፡

‘’በቂ ናቸው ባይባልም በአዲስ አበባ ከተማ በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ እየተሻሻሉ የመጡ በዙ አሰራሮች አሉ’’ ሲሉ የተጠቀሱት ወ/ሮ አየሁ፤ በአሁን ሰዓት በከተማዋ ያሉ አካል ጉዳተኞች መብታቸው እየተከበረላቸው ነው ወይ የሚለው ግን እርሳቸው መመለስ የሚችሉት እንዳልሆነም አስረድተዋል፡፡


‘’ራስ አገዝ አሰራር ድርጅቶች ህብረት’’ (Consortium Of Self Help Group Approach Promoters) የተለያዩ ድርጅቶች በህብረት ሆነው የመሰረቱትና በአካል ጉዳተኛ ሴቶችና በህፃናት ላይ የሚሰራው ድርጅት ነው፡፡


የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ዮሴፍ አካሉ፤ በአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር በኩል በተነሳው ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ ስንል ጠይቀናቸዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page