top of page

ታህሣስ 2፣2017 - በትግራይ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ17,000 በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውን ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Dec 11, 2024
  • 2 min read

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የወባ ወረርሽኝ በስፋት እየታዬ እንደሆነ ይነገራል፡፡


ካለፈው ሁለት ዓመታት በተለየ የወባ ወረርሽኝ ቁጥር መጨመሩን የተለያዩ ቁጥራዊ መረጃዎችም ያሳያሉ፡፡


ለምሳሌም በትግራይ በ2016 ዓ.ም ጥቅምት ወር በሳምንት ከ10,000 በላይ ሰዎች በወባ ወረርሽኝ ሲያዙ እንደነበር የተነገረ ሲሆን በተያዘው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር ሥርጭቱ ሰፍቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ17,000 በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውን ሸገር ከክልሉ ጤና ቢሮ ሰምቷል፡፡


ከጥር ወር 2016 ዓ.ም እስከ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአጠቃላይ በክልሉ በወባ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ300,000 በላይ መሆኑን ሪፖርት ያሳያል የሚሉት አስተባባሪው ይህም ከዚህ ቀደም ታቶ የማይታወቅ እና ቁጥሩም ከፍተኛ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል፡፡

በወረርሽኙ ምክንያት 18 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ከጤና ቢሮ ሰምተናል፡፡


ወረርሽኙ እንደ ክልል ብቻ ሳይሆን እንደሀገር እየጨመረ መምጣቱ በተደጋጋሚ ሲነገር ሰንብቷል፡፡


በዚህም በአማራ ክልል የወባ ወረርሽኝ ስርጭት መጨመሩ የተነገረ ሲሆን ከ600,000 በላይ ሰዎችም በወረርሽኙ መያዛቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ካሳለፍነው ሀምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም ወር ብቻ የተገኘ መሆኑን ሰምተናል፡፡


በወረርሽኙ ከሚያዙ ህሙማን ቁጥር በተጨማሪ የሟች ቁጥርም እስካሁን ድረስም ካሳለፍነው ሀምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሶስት ወራት ውስጥ 37 መድረሱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡


የወባ ወረርሽኝ ስርጭት ከታየባቸው ክልሎች ሌላኛው ደግሞ ኦሮሚያ ሲሆን ከ358 ወረዳዎች 329ኙ ላይ የወባ በሽታ መኖሩን የሰማን ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 132 ወረዳዎች ላይ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንዳለ ተነግሯል፡፡


በኦሮሚያ ክልል 39.5 ሚሊየን ህዝብ ለወባ ወረርሽኝ ተጋላጭ ነው የተባለ ሲሆን 4.3 ሚሊየኑ የወባ ምልክት ያሳዩ እና ህክምና ያገኙ ናቸው ተብሏል፡፡


በዚህም መሰረት 2017 ዓ.ም በተደረገ ክትትል 1.9 ሚሊየኑ የክልሉ ነዋሪ የወባ በሽታ የተገኘበት መሆኑን ሰምተናል፡፡


ከዚህ ቀደም እየጠፉ ያሉ እንደወባና ኮሌራ ያሉ በሽታዎች በወረርሽኝ መልኩ የሚከሰቱት ግጭት ባለባቸው አካባቢ በመሆኑ ሰብአዊ ቀውሱ እንዳይባባስ በአካባቢዎች የህክምናው ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠውም የተለያዩ አካላት እያሳሰቡ ነው፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page