top of page

ታህሣስ 1፣2017 - የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከተጀመሩ ከ10 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ፕሮጀክቶችን ለምን ማጠናቀቅ እንደተሳነው ተጠየቀ

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከተጀመሩ ከ10 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለምን ማጠናቀቅ እንደተሳነው በፓርላማ አባላት ተጠየቀ፡፡


ባለው ባየ (ዶ/ር) የተባሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በአማራ ክልል #ደቡብ_ጎንደር ዞን ፎገራ የሚገኘው የረብ ግድብ ከተጀመረ ከ15 ዓመት በላይ እንደሆነው አስታውሰው መቼ አንደሚጠናቀቅ ጠይቀዋል፡፡


የምክር ቤት አባሉ ፕሮጀክቱ ካለመጠናቀቁም በላይ የግንባታው አፈጻጸሙ ዝቅተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለተለያዩ አካላት ብናሳውቅም ችግሩን የሚፈታልን አካል ማግኝት አልቻልንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡


መሬታቸውን ለልማቱ የለቀቁ አርሶ አደሮችም ፕሮጀክቱን እንደ እርግማን ነው እየወሰዱት ያሉት ሲሉ ዶ/ር ባለው ባየ አስረድተዋል፡፡


አሁን ላይ ፕሮጀክቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጥሯል ያሉት የምክር ቤት አባሉ ችግሩ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡


ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ #የረብ_የመስኖ_ፕሮጀክት 45 በመቶ ተሰርቶ አሁን ላይ ግንባታው በፀጥታ ምክኒያት ቆሟል ብለዋል፡፡


ሌላው ጥያቄ #የኦሞ_ኩራዝ መስኖ ፕሮጀክትን የተመለከተ ነው ጠያቂዋም መሰረት ማዲሎ የተባሉ የምክር ቤት አባል ናቸው፡፡

ጠያቂዋ የኦሞ ኩራዝ የመስኖ ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ እየተባለ በተከታታይ በጀት በምክር ቤቱ ጸድቋል ይሁንና አሁንም በተባለው ልክ ፕሮጀክቱ እየተሰራ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የፓርላማ አባላቱ በተለያዩ ጊዜያት ተጀምረው የቆሙ ዓመታትን ያስቆጠሩ ፕሮጀክቶች ለምን እንዳልተጠናቀቁ ጠይቀዋል፡፡


የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በበኩሉ በእግባቡ ዲዛይናቸው ሳይጠና እና በቂ ዝግጅት ሳይደርግባቸው በችኮላ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በመሆናቸው ለማጠናቀቅ አስቸጋሪ ሆኗል ብሏል፡፡

መስሪያ ቤቱ በ8 ቢሊዮን ብር በጀት የ40 ቢሊዮን እንደሰራ መጠየቄ አግባብነት የለውም ብሏል፡፡

የበጀት አጥረትም ሌላኛው እንቅፋት መሆኑን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ ተናግረዋል፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አሁን ላይ 120 ቢሊዮን ብር የሚወጡ ፕሮጀክቶችን እየፈጸምኩ ነው ብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page