አስር ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ‘’ልዩ የኢኮኖሚ ዞን’’ ማደጋቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መናገሩ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ፓርኮቹ ያሉበትን ደረጃ በመገምገም ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት ለማደግ 10ሩ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላታቸው ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት እንዲያድግ ወስኛለው ብሏል፡፡
ለመሆኑ የፓርኮቹ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ማደግ ያለው ፋይዳ ምንድነው?
የምጣኔ ሃብት ባለሞያ የሆኑትን አቶ ክቡር ገናን እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንን ጠይቀናል፡፡
የምጣኔ ሃብት ባለሞያው አቶ ክቡር ገና የፓርኮቹ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ማደጋቸው ያለውን ተስፋ እና ስጋት ነግረውናል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበኩሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማደግ ለአርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ የገበያ ትስስር የሚፈጥር መሆኑን የኢኮኖሚ ሽግግር ለማድርግ እንደሚረዳ የተሻለ እና ጥራት ያለው ምርት ለማምረት ብሎም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ይረዳል ብሏል፡፡
ለባለሃብቱ የሚኖረውን ፋይዳም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ነግሮናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments