top of page

ታህሣስ 1፣2017 - በአዲስ አበባ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ (UNISA) አስካሁን ካስመረቃቸው ተማሪዎቹ 330ዎቹ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምህሩ መምህራን ናቸው አለ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ (UNISA) አስካሁን አስተምሮ ካስመረቃቸው ተማሪዎቹ 330 የሚሆኑትበኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምህሩ መምህራን ናቸው አለ።


#UNISA በኢትዮጵያ መንግስትና በደቡብ አፍሪካ መንግስት ትብብር አማካይነት በኢትዮጵያ ከተከፈተ 15 ዓመት እንደሆነው ሰምተናል።


በእነዚህ 15 ዓመታት ዩኒቨርስቲው 1,099 ተማሪዎቹን አስተምሮ ማስመረቁን የዩኒቨርስቲው የኢትዮጵያ ትምህርት ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር አቶ መሰረት መለሰ ነግረውናል።


ከተመራቂዎቹ መካከል 50 በመቶዎች PhD፣ 40 በመቶዎቹ ማስተርስ ዲግሪ ቀሪዎቹ 10 በመቶዎች ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

ከዩኒቨርሲቲው የ15 ዓመታት ተመራቂዎች ውስጥ 330 ዎቹ የPhD ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ #መምህራን መሆናቸውን ያስታወሱት አቶ መሰረት ከእነዚህም ውስጥ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑ ይገኙበታል ብለዋል።


ዩኒቨርሲቲው ሰሞኑንም 59 በPhD እንዲሁም 3 በማስተርስ ዲግሪ በድምሩ 62 ተማሪዎቹን አስመርቋል።


ህብረተሰብ ጤና፣ ትምህርት፣ ቢዝነስ፣ ህግ እና ሌሎች ተማሪዎቹ የተመረቁባቸው የትምህት ዘርፎች መካከል ይገኙበታል ።


በአዲስ አበባ በሚገኘው የደቡብ አፍሪካው የመንግሰት ዩኒቨርስቲ ዩኒሳ ገብተው የሚማሩ #ተማሪዎች የሚከፍሉት የትምህርት ክፍያ ልክ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች በሀገራቸው ባለው የዩኒቨርስቲው ዋና ካምፓስ የሚከፍሉትን ያህል መሆኑንም አቶ መሰረት ነግረውናል።


ዩኒቨርሲቲው በአዲስ አበባ የተከፈተው በመንግስት ለመንግሥት ትብብር በመሆኑ የትምህርት ክፍያው ዝቅተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ ተማሪዎች የመመረቂያ ጥናታቸውን ሲሰሩ ተወዳድረው የሪሰርች ገንዘብ ይሰጣቸዋል ተብሏል።


ከUNISA ተመራቂዎች መካከል ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ተመራማሪዎች፣ የባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች፣ በፖሊስ እና በጤና ተቋማት የሚሰሩ እንደሚገኙበት አቶ መሰረት ነግረውናል።


በአዲስ አበባ ቅርንጫፉን ከከፈተ 15 ዓመት ያስቆጠረው የደቡብ አፍሪካው የመንግስት ዩኒቨርስቲ UNISA ከተመሰረተ 150 ዓመት ሞልቶታል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page