ታህሣስ 1፣2017 - ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም እግድ ጥሎባቸው ከነበሩ ፖርቲዎች መካከል የአምስቱን እግድ ማንሳቱን ተናገረ
- sheger1021fm
- Dec 10, 2024
- 1 min read
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም እግድ ጥሎባቸው ከነበሩ ፖርቲዎች መካከል የአምስቱን እግድ ማንሳቱን ተናገረ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም 11 ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሣኔ አስተላልፎባቸው እንደነበረ የታወሳል፡፡
ፓርቲዎቹ እግድ ተላልፎባቸው የነበረው፤ ከጠቅላላ ጉባዔ፣ ከኦዲትና በሴት አባላት ቁጥር አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተገናኘ ነበረ፡፡
በወቅቱ እግድ ከተጣለባቸው 11 ፓርቲዎች አሁን ላይ የአምስቱ ዕግድ አንስቻለሁ ብሏል ቦርዱ፡፡
ፓርቲዎቹ እግዱ የተነሳላቸው የይቅርታና የመከላከያ መልስ በማቅረባቸው ነው ተብሏል፡፡
ምርጫ ቦርድ ዛሬ እግዳቸውን አንስቼላቸዋለሁ ያላቸው ፓርቲዎች፤
1. የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎ.ብ.ን)፣
2. አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አ.ት.ፓ)፣
3. የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋ.ህ.ዴ.ን)፣
4. የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት (ኢ.ዴ.ህ) እና
5. የአገው ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ናቸው፡፡
ፓርቲዎቹ ያለፈውን ስህተት እንደማይደግሙና በቀጣይም የቦርዱን ሥራ ከሚያደናቅፍና ዕምነት ጥያቄ ውስጥ ከሚከቱ ተግባራት ተቆጥበው እንዲቆጠቡ በማሳሰብና በማስጠንቀቅ ዕግዱን ማንሳቱን ተናግሯል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም እግድ ጥሎባቸው የነበሩና አሁን እግዱ ተነስቶላቸዋለሁ ከተባሉት ዝርዝር ውስጥ የሌሉት ፓርቲዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣
2. አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፖርቲ፣
3. ጌዲኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣
4. የሐረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣
5. የገዳ ሥራዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ እና
6. የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ናቸው።
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments