top of page

ባለሞያ ቀጥረው ለመከራከር አቅም ለሌላቸውና መንግስት ነፃ የህግ አገልግሎት የሚሰጣቸው ሰዎች

  • sheger1021fm
  • Nov 19, 2025
  • 1 min read

ህዳር 10 2018

 

በፍርድ ቤቶች ጠበቃ አቁመው የህግ ባለሞያ ቀጥረው ለመከራከር አቅም ለሌላቸው ሰዎች መንግስት ነፃ የህግ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

 

ነፃ የህግ አገልግሎት በተለይም በሴቶች፣ በህፃናት፣ በአካል ጉዳተኞችና በአረጋዊያን ላይ ትኩረት እንደሚያደረግ በፍትህ ሚኒስቴር የንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ አቃቢ ህግ አቶ ተሰማ ግደይ ነግረዉናል፡፡

 

ዐቃቢ ህጉ ባለፉት 3 ወራት ውስጥ በፍትህ ሚኒስቴር  178 ፤ በጠቅላይ ፍ/ቤት ደግሞ ከ1300 በላይ ሰዎች ነፃ የህግ አገልግሎት አግኝተዋል ብለዋል፡፡

 

ይህም ፍትህ እንዳይጓደል፣ ድሃ እንዳይበደል፣ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው የሚለውን  መርህ ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ አቶ ተሰማ ጠቁመዋል፡፡

 

ይሁን እንጂ ነፃ የህግ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ሀላፊነት የሚሰጣቸው የህግ ባለሙያዎች ክርክሩን የሚያደርጉት ያለ ምንም ክፍያ በመሆኑና የፍርድ ቤት ክርክሮች ደግሞ በባህሪያቸው ውስብስብና ብዙ ድካምን የሚጠይቁ ከመሆናቸው አንፃር ፍትህን ለማስፈን እስከ ምን ድረስ ይሄዳሉ? የሚለው ለብዙዎቹ ጥያቄ ይሆናል፡፡

 

ከፍተኛ ዐቃቢ ህጉ አቶ ተሰማ ግደይ ግን መልስ አላቸው፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page