top of page

በ2018 በጀት ዓመት 9 ወራት 103 አዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡

  • May 4
  • 1 min read

ሚያዝያ 26/2018


በ2018 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 103 አዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡


አገልግሎቱ ከዋናው ግሪድና ከግሪድ የራቁ በርካታ አዳዲስ አካባቢዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን እና ከጤናና ማህበራዊ ተቋማት በተጨማሪ ከ31 ሺህ በላይ አባዎራዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡

በዚህም 82ቱ ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ (ግሪድ) እንዲሁም 21 የገጠር ከተሞችና መንደሮችን ደግሞ በፀሃይ ኃይል አማራጭ (ኦፍግሪድ) የተገናኙ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡



በተጨማሪም 423,200 አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ያለ ሲሆን ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ18 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል፡፡


ኃይል ከተገናኘላቸው አዳዲስ ደንበኞች ውስጥ 31 ሺህ 298 ያህሉ አዲስ የኤሌክትሪክ ተደራሽ በሆኑት የገጠር ከተሞችና መንደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡


አዲስ ኤሌክትሪክ ካገኙ ደንበኞች መካከል 74.2 ከመቶ የድህረ ክፍያ እንዲሁም 25 ነጥብ 8 በመቶ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ናቸው፡፡


በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞች ቁጥር 5.64 ሚሊዮን ደርሷል መባሉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳያል ፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page