top of page

''በጤናና በግብርና ሚ/ር ስር ያሉ 22 ተጠሪ ተቋማት ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከተ የሚሰሩት ስራ አጥጋቢ አይደለም'' በሚል ተተቹ

  • sheger1021fm
  • Jan 2
  • 1 min read

ታህሳስ 24/2018 

 

በጤና እና በግብርና ሚኒስቴር ስር ያሉ 22 ተጠሪ ተቋማት ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋዊያንን እና ሌሎች ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከተ የሚሰሩት ስራ አጥጋቢ አይደለም በሚል ተተቹ፡፡

 

ትችቱን ያቀረበው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።

 

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በስርዓተ ጾታና በማህበራዊ አሳታፊነት ወይም አካቶ ዙርያ በ22 የጤና ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ላይ ያደረገውን የምዘና ውጤት ይፋ አድርጓል።

 

ተቋማቱ የተመዘኑትም የሴቶችን፣ የሕፃናትን ፣ የወጣቶችን፣ የአካል ጉዳተኞችን፣ የአረጋዊያንን እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጉዳዮች በስራዎቻቸው ምን ያህል አሳትፈዋል? ምን ያህልስ ተጠቃሚነታቸውን አረጋግጠዋል? በሚል ነው። 

ምዘና ከተደረገባቸው ተቋማት ዉስጥ አብዛኞቹ ዝቅተኛ አፈፃፀም እንዳስመዘገቡም ተነግሯል።

 

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር እርጎጌ ተስፋዬ   ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በስራዎቻቸው በበቂ ሁኔታ ያላሳተፉ ተቋማት ብዙ ናቸው ብለዋል።

 

ይህም የሆነበት የአመራር ቁርጠኝነት ማነስ፣ የተጠያቂነት ስርዓት አለመስፈን፣ የተቋማት የጋራ ትብብር አለመኖርና በመሰል ችግሮች እንደሆነም ነግረውናል።

 

ሚኒስትሯ አክለውም  ከዚህ ቀደም ምዘና የተደረገባቸው ተቋማት ማሻሻል ያሳዩ ቢሆንም አጠቃላይ የምዘናው ውጤት የሚያሳየው መስሪያ ቤቶች ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማሳተፍን ወይንም አካቶን በውል እንዳልተረዱት ነው ይላሉ።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page