በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች በጦርነት ምክንያት የባንክ እዳችን የሚሸጋሸግበት መንገድ ባለመኖሩ ተቸግረናል አሉ፡፡
ባለሀብቱ በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው የቡላላ ዲኒኬት እርሻ ንግድና ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ምክትል ስራ አስኪያጅ ሮማን እሸቴ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
ጦርነትና ግጭት ግን ባለሀብቱ አምርቶ ምርታማ እንዳይሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡
ኢንቨስተሩ በችግር ውስጥ ሆኖም ስራው እየሰራ ከባንኮች የተበደረው ብድር በወቅቱ እንዲመልስ ይጠበቅበታል፡፡
በጦርነት ምክንያት የሚባክኑ ጊዜያት እየታየለት አይደለም ይህ ደግሞ ስራ ሳይሰራ እዳ ብቻ እንዲከፍል እያደረገው መሆኑን ነግውናል፡፡
አፍሪካ አግሪ ቢዝነስ አካዳሚ ኢትዮጵያ ውስጥ የግብርና ገበያን በተመለተ ባስጠናው ጥናት የግልብ ባለሀብቱ በግብርናው ዘርፍ ላይ ያለው አስተዋፅኦ ተመልክቷል፡፡
በ1991 እና 92 አካባቢ በኢትዮጵያ የግል ባለሀብቱ በሰፋፊ የግብርና እርሻ ላይ ተሳትፏቸው 12 ከመቶ እንደነበር ጥናቱ ያሳያል፡፡
ይህ ቁጥር አሁን ላይ ወደ 1 ከመቶ ዝቅም ብሏል፡፡
የአካዳሚው ኃላፊ ኤልያስ ገነቴ እንደተናገሩት አሁን በግል ባለሀብቱ የሚተዳደረው ሰፋፊ እርሻ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቶ 1 ከመቶ ደርሷል፡፡ ይህም የሆነው የሚደረገው ድጋፍ አበረታች ስላልሆነ ነው፡፡
በሀገሪቱ ህግ ላይ ለባለሀብቶች የሚደረጉ ማበረታቻዎች ቢጠቀሱም መሬት ላይ ግን እየተተገበሩ አይደለም፡፡
አቶ ኤልያስ እንደሚሉት ከሆነ በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ ውስጥ የተከሰቱ ጦርነቶች ባለሀብቱ በአንድ ጀንበር ያፈራው ንብረት ለውድመት ዳርጎበታል ይህ ደግሞ ብዙዎችን ከስራው እንዲወጡ እያደረገ ነው፡፡
በተለይም የውጪ በለሀብቶች አንድ ችግር ሲፈጠር በፍጥነት ሀገር ጥለው ይወጣሉ፡፡ አበዳሪዎቹ ባንኮች ባለሀብቱ ተበድሮ ንብረቱ በጦርነት ሲወድምበት በምን መንገድ ማስተናገድ እንዳለባቸው የሚመራ ህግ የላቸውም፡፡
ታዲያ አሁን መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቼ እየሰራሁ ነው ባለሀብቶችንም እየደገፍሁኝ ነው ይላል
እውነት መንግስት እንዳለው እየደገፋቸው ነው ወይ ስንል ጠይቀናል፡፡
በረከት አካሉ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments