top of page

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አሳሰበ።

  • Jun 25
  • 1 min read

ሰኔ 18/2018


በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት አዝማሚያ ስላለ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ አሳሰበ።


በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለና ከመንግስት ጋር አስፈላጊውን ግንኙነት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።


የደቡብ አፍሪካ መንግስት በስደተኞች ላይ የኃይል ጥቃቶች እንዳይደርሱ በሁሉም አካባቢዎች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ አስታውሷል።

ሁሉም ጉዳዮች በህጉ መሰረት እንደሚከናወኑ እና በቀጣይም የሀገሪቱ መንግስት የፀጥታ ማስከበር ተግባሩን እንደሚያጠናክር ኤምባሲው በመግለጫው ተናግሯል።


በዚህም በስደተኞች ላይ ህገ ወጥ ድርጊት እና ጥቃቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት ሁኔታዎች መታየታቸውን ኤምባሲው አስረድቷል።


ስለዚህም በመላው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በስደተኞች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የመብት መጣስ መሰረት በማድረግ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲያደርጉ አሳስቧል።


ከሚኖሩበት አካባቢ የመንግስት አካላት እና የኮሚኒቲ አደረጃጀቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲያደርጉ፣መረጃዎችንም እንዲለዋወጡ እንዲሁም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page