በከባድ የሰዎች ዝውውር እና በ4 ቢሊዮን ብር ማሸሽ ወንጀል የተከሰሱት እነ ይትባረክ ዳዊት ላይ በቀረበው መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡
- Jun 30
- 1 min read
ሰኔ 23/2018
በከባድ የሰዎች ዝውውር እና በ4 ቢሊዮን ብር ማሸሽ ወንጀል የተከሰሱት እነ ይትባረክ ዳዊት ላይ በቀረበው መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡
በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በሰው መነገድ እና በገንዘብ ማሸሽ ( #Money_Laundering ) ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
ተከሳሾቹ ቁጥራቸው 11 ሲሆን ስድስቱ በቁጥጥር ስር ውለው የዋስትና መብታቸው ተነፍጎ ማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን እየተከታተሉ ነው።
ቀሪዎቹ 5ቱ ግን በሌሉበት ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ይገኛል።

ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ባቀረበው 16 ክሶች በዋናነት ከኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ እስከ ሱዳንና ሊቢያ የሚደርስ ዓለም አቀፍ የወንጀል ቡድን በማደራጀት በበላይነት ሲመሩ ቆይተዋል።
ወደ አውሮፓ በመሻገር የተሻለ ሥራ እንደሚያገኙ በማሳመን ተጎጂዎችን በማጓጓዝ፣ በመተማ በኩል አሻግረው ሱዳንና ሊቢያ በሚገኙ መጋዘኖች ውስጥ በማሰር ከፍተኛ ስቃይ አድርሰዋልም ይላል የክስ ዝርዝሩ።
ተጎጂዎችን በማሰቃየት የተቀረጹ ቪዲዮዎችን ለቤተሰቦቻቸው በመላክ፣ ከእያንዳንዳቸው ከ750 ሺህ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ በከባድ የስነ-ልቦና ጫና ሲያስገደዱ ቆይተዋል የሚሉት ይገኙበታል ።
በአጠቃላይ ከ2015 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ 3 ሺህ 800 የሚሆኑ ተበዳዮችን በማገት፣ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ከቤተሰቦቻቸው ሰብስበዋል የሚሉት ክሶች ተካተዋል።
ከዚህ በፊት በነበረው ችሎት በተከሳሽ ጠበቆች አማካኝነት የክስ መቃወሚያ ቀርቦ የነበር ሲሆን ዛሬ በዋለው ችሎት ዐቃቢ ህግ ለመቃወሚያው በፅሁፍ መልስ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ተከሳሾቹ ከ3,800 በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማዘዋወር፣ 133 ሰዎችን ለሞት በመዳረግ እና 116 ሴቶችን እንዲደፈሩ ምክንያት ናቸው በሚል እና በሌሎች ጉዳዮች ተጠርጥረው በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለው ዐቃቢ ህግ 16 ክሶችን ከመሠረተባቸው ከ3 ወር በላይ ሆኗቸዋል።





That's a heavy story about trafficking and money laundering—really scary stuff. When I need a break from heavy news, I edit my pics with ai image editor it’s fast and fun.