በኤልኒኖ ምክንያት ሊከሰት ይችላል የተባለውን የድርቅ ስጋት
- May 21
- 1 min read
ግንቦት 13/2018
መጪው ክረምት በኤልኒኖ ምክንያት ሊከሰት ይችላል የተባለውን የድርቅ ስጋት የሚመለከታቸው ተቋማት ለገበሬው እና ሌላም ጉዳዩ ለሚያገባቸው መረጃውን እንዲያደርሱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
መረጃውን ከማድረስ ባሻገር አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ሳያደርጉ ቀርተው ጉዳት ከተከሰተ ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር መዘርጋቱን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (IGAD) ተናግሯል፡፡
የዘንድሮው የክረምት ዝናብ ጥሩ አጀማመር ቢኖረውም በነሃሴ እና መስከረም ወራቶች ግን ደረቅ ሰሞናት ሊበዙ ፤
የዝናብ መዋዠቅ እና መቆራረጥም ሊታይ እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሊጂ ኢንስቲትዩት ከሠሞኑ ይፋ ባደረገው ትንበያው ማሳወቁ ይታወሳል።
ይኖራል ተብሎ የተተነበየው ደከም ያለ የኤልኒኖ ክስተት በነሃሴ እና መስከረም ወራቶች ደረቅ ሰሞናት እንዲበዙ ፤
ብሎም የዝናብ መዋዠቅ እና መቆራረጡ እንዲያጋጥም የሚያደርግ ምክንያት ነው ተብሏል።
የኤልኒኖ ክስተት ታየ ማለት ግን ወዲያውኑ ድርቅ ይከሰታል ማለት እንዳልሆነ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሣምነው ተሾመ ተናግረዋል።
ከክረምቱ በፊት እየጣለ ያለው የበልግ ወቅት ዝናብ በመደበኛ ሁኔታ የቀጠለ በመሆኑ ኤልኒኖ የሚከሰትባቸው አካባቢዎችም ቢሆኑ፤ ያን ያህል ይጎዳሉ የሚል ግምት እንደሌለ ዶክተር ዶክተር አሣምነው ተናግረዋል።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት የአደጋ መከላከል ሃላፊ ዶክተር አህመድ አምድይሁን በበኩላቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ የአካባቢው ሀገራት ትንበያዎችን መሰረት አድርገው ተገቢውን የቅድመ መከላከል ስራ እንዲሰሩ ፤ ሳይሰሩ ቀርተው ጉዳት ከደረሰ ግን ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርአት በጋራ ስምምነት ተፈጥሯብለዋል።
ትንበያዎች ከዚህ ቀደምም ይሰጡ እንደነበር ያስታወሱት ዶክተር አህመድ በዚያው ልክ ጉዳቶችም ይደርሱ ነበር ብለዋል።
የዚህ ችግሩ ትንበያዎቹን መሰረት ያደረገ የቅድመ መከላከል ስራ አለመሰራቱ እንደሆነ ተናግረዋል።
አሁን ግን የቅድመ መከላከሉን ስራ አለመስራት ተጠያቂነትን ያስከትላል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሊጂ ኢንስቲትዩት በነሃሴ እና መስከረም ወራቶች ደረቅ ሰሞናት ሊበራከቱባቸው እንዲሁም ፤
የዝናብ መዋዠቅ እና መቆራረጥ ሊያጋጥምባቸው ይችላል ያላቸው በዋናነት የሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎችን ነው።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments