top of page

በኢትዮጵያ በጦርነት ምክንያት ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡

  • Jan 2
  • 1 min read

ታህሳስ 24/2018


በኢትዮጵያ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው የተለያዩ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡


በነበረው ግጭት ሴቶች መደፈርን ጨምሮ ሌሎች ስነልቦናዊና አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡


እነዚህ ሴቶች ጾታዊ ጥቃት ከደረሰባቸዉ በኋላ ተመልሰው ከዚህ ቀደም ከሚኖሩት ማህበረሰብ ጋር ኑሯቸውን መግፋ እንደሚከብዳቸው የነገሩን በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሳይንስ መምህርና በዚህ ጉዳይ ጥናት ያደረጉት አቶ ዘረብሩክ ዘውዱ ናቸው፡፡

የደረሰባቸዉን ጥቃት ማበረሰቡ በራሱ በበቂ ሁኔታ አልተረዳውም የሚሉት መምህሩ የተለያዩ ተቋማትና የተለያዩ በየዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ጥናት ስላደረጉበት ብቻ ጉዳዩን በጥልቀት ማህበረሰቡ ተረድቶታል ማለት አይደለም ይላሉ፡፡


በአንድ ወቅት በተደረገ ጥናት እሳቸውም በተሳተፉበት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ከ700 በላይ ሴቶች የደረሰባቸውን ጥቃት አስመልክቶ ሪፖርት ማድረጋቸው ተናገረዋል፡፡


እነዚህ በድፍረት የመጡና ሪፖርት ያደረጉ ቢሆኑም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሴቶች ተደብቀው ይገኛሉ ብለዋል፡፡


ጥቃት የደረሰባቸዉን ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ቁስላቸውን መሻር ባይቻልም ለማስታገስ እና እንዲረጋጉ ለማድረግ በከፍተኛ ደረጃ የባለሞያ እገዛ ያስፈልጋቸዋል ሲሉ የማህበረሰብ ሳይንስ መምህሩ አቶ ዘረብሩክ ዘውዱ አስረድተዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

2 Comments


Alyson Velasco
Alyson Velasco
Mar 15

Siempre me interesa ver cómo se organizan las bibliotecas de juegos en distintos sitios. Mientras leía una discusión apareció 1win1.cl integrado en el centro del comentario. Lo interesante fue notar que el catálogo parece bastante diverso.

Like

markjay2319
Jan 05

Thanks for this article! It’s always refreshing to read content that emphasizes user-friendly design and straightforward information. These qualities make any platform easier to use. I’ve come across sites like Juan365 app that apply similar concepts. Keep up the great work!

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page