top of page

በኢትዮጵያ በተለያዩ የትምህርት ተቋማት እንደሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች

  • Jul 1
  • 1 min read

ሰኔ 23 2018


በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ14,000 በላይ ጥናቶች እና ምርምሮች በተለያዩ የትምህርት ተቋማት እንደሚደረጉ ይነገራል።


ከእነዚህ ጥናቶችና ምርምሮች ስራ ላይ ውለው የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እያገዙ ያሉት ግን ጥቂቶቹ ናቸው ተብሏል።


ጥናቶቹ የህብረተሰቡን ችግር መነሻ አድርገው አለመካሄዳቸው እና በጋራ መድረክ አለመገምገማቸው የችግሩ መነሻ እንደሆነ ተጠቅሷል።

በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በተማሪዎች እና በምሁራን እንዲሁም በተመራማሪዎች የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች በአንድ መድረክ ቀርበው ውይይት ቢደረግባቸው መፍትሄ ያመጣሉ ተብሏል።


ይህ የተባለው ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ባካሄደው 18ተኛው የዘርፈ ብዙ ጥናት እና ምርምር ጉባኤ ላይ ነው።

በጉባኤው በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በቢዝነስ እና ኢንድስትሪ በፋይናስ በግብርና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተመለከተ እንዲሁም ቴክኖሎጂን የተመለከቱ ጥናት እና የምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።


እንደዚህ ዓይነት የመመረቂያ እና በምሁራን የሚቀርቡ ጥናት እና ምርምሮች በተናጠል ከሚቀርብ በጋራ በአንድ ላይ ቢደረጉ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚመጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዉይይት ቢደረግባቸው ችግር ፈቺ የመሆን ዕድላቸው ሰፊ ነው መባሉን ሰምተናል።


የጥናት እና ምርምር ውጤቶቹ ለፖሊሲ ግብአት እንዲሆኑ የሚመለከታቸው ጋር ማድረስ ያስፈልጋል ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..


ማርታ በቀለ

1 Comment


镇华 莫
镇华 莫
Jul 03

Great read on the hurdles of distance learning in Ethiopia—really shows how important planning is. If you’re trying to figure out study dates, a weeks from now calculator can help you see exactly when your next deadline falls.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page