በኢትዮጵያ ለሚፈጠሩ ግጭቶች፤ የተዛቡ ትርክቶች እንደ ምክንያት ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡
በኢትዮጵያ የበዳይና ተበዳይ፣ የጠፊና አጥፊ፣ የጨቋኝና ተጨቋኝ፣ የገዢና ተገዢ ትርክቶች፤ ላለው የሰላም እጦት እንደ ምክንያት ይነሳሉ፡፡
‘’ፅናት ለኢትዮጵያ’’ እና ‘’ሰላም አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር’’ የተሰኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ባሰናዱት የምክክር መድረክ ላይ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር የሺጥላ ወንድሜነህ፤ ስለ ትርክት ምንነት ስለሚያመጧቸው ጉዳቶች እና ማን እንደሚፈጥራቸው ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
ትርክት ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ ‘’ትርክት ክስተቶችን ወይም ፅንሰ ሐሳቦችን ለማብራራት፣ ለመተርጎም የሚገነባ ብዙ ጊዜ የተለያዩ አመለካከት በተለይም የአፈነገጠ አመለካከት፣ ሀሳብን የሚያንፀባርቅ አንድ ወጥ ታሪክ ወይም መለያ ነው’’ የሚል መልስ ይሰጣሉ፡፡
ትርክቶች በማን ይፈጠራሉ የሚለው ደግሞ ‘’ትርክቶች በፖለቲከኞች፣ በልሒቃን፣ የሃይማኖት ቡድኖች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ማህበራዊ አንቂዎች ትርክት ፈጣሪዎች’’ መሆናቸውን ያስረዳሉ፡፡
ትርክቶችን በመፍጠር ፖለቲከኞችና ሊዕቃን ግን ትልቁን ድርሻ እንደሚይዙ አስረድተዋል፡፡
ትርክት ፈጣሪዎች ትርክቶችን የሚፈጥሩበት ምክንያት ደግሞ የሚፈልጉትን የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸው ተቀባይነት እንዲኖረው ስሜት በሚገዛ መልኩ ትርክቶችን እንደሚቀርፁ ያስረዳሉ፡፡
ማንነትን ለመገንባት እና ነባሩን ገዢ ትርክት ለመግደርደር የሚፈጠሩ ትርክት መኖራቸውንም ፅሁፍ አቅራቢው ነግረውናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments