top of page

በአዲስ አበባ 21 የቅጥር ኤጀንሲዎች መታገዳቸው ተሰምቷል

  • Jun 17
  • 1 min read

ሰኔ 10/2018


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተያዘው በጀት ዓመት ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው የቅጥር ኤጀንሲዎች መካከል 21ዱ መታገዳቸው እና ፤ የ3ቱ ደግሞ ፍቃዳቸው መሰረዙ ተሰምቷል፡፡


100 የሚሆኑ ኤጀንሲዎች ደግሞ ስራቸውን በአግባቡ አልከወኑም ህጋዊነትንም አልተከተሉም ተብለው ጉዳቸው በቢሮው የማኔጅመንት እየታየ ይገኛል ተብሏል።


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበውና ፈቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ ወደ 384 የሚጠጉ የሰራተኛና አሰሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች ይገኛሉ።


የእነዚህ ኤጀንሲዎች ኃላፊነት ከተሰጣቸው ኃላፊነት ውጭ የሚሰሩ፣ ለሰራተኞች ተገቢውን ደመወዝ የማይከፍሉ፣ እንዲሁም ሰራተኞች ዓመታዊና የወሊድ ፈቃድ በሚወስዱበት ወቅት ደመወዝ የሚቀንሱ ኤጀንሲዎች ላይ ከዕገዳ እስከ ፈቃድ ስረዛ የሚደርስ ጥብቅ እርምጃ እየተወሰደ ነው ተብሏል።


በበጀት ዓመቱ በተደረገው ቁጥጥርና ክትትል፣ ህጉን ተከትለው ባልሰሩ 21 ኤጀንሲዎች ላይ የእግድ እርምጃ መወሰዱን በአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የስራ ስምሪት ፈቃድ ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ በላይ ተሰማ ነግረውናል።


ድርጅቶች ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲሰሩ፣ ፈቃዳቸውን ሳያድሱ ሲቀሩ ወይም የሰራተኛ መብት መጣሳቸው በክትትልና በጥቆማ ሲደረስበት መጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል ያሉት አቶ በላይ ነገር ግን ተነግሯቸው ስህተታቸውን ካላስተካከሉ ፈቃዳቸውን እስከመንጠቅ የሚደርስ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።


በዚህ አግባብም 3 ኤጀንሲዎች ፈቃዳቸው ሙሉ በሙሉ ተነጥቋል።


100 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳያቸው በቢሮው ማኔጅመንት እየታየ እንደሚገኝ ነግረውናል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…

ገዛ ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…









Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page