በአዲስ አበባ የነዳጅ ማደያዎች ተሰፍሮ የተሰጣቸውን ነዳጅ ከስፍር እያጎደሉና እየሰረቁ ማስቸገራቸው ተነግሯል፡፡
- Aug 5
- 1 min read
ሐምሌ 29 2018
በአዲስ አበባ የነዳጅ ማደያዎች ተሰፍሮ የተሰጣቸውን ነዳጅ ከስፍር እያጎደሉና እየሰረቁ ማስቸገራቸው ተነግሯል፡፡

ከ133 ማደያዎች ለተጠቃዎች በታማኝነት ከሊትር ያልጎደለ ነዳጅ የሚሸጡት 42 ብቻ መሆናቸውን የከተማዋ ንግድ ቢሮ ተናግሯል፡፡
በዚሁ ምክንያት ከስራ እስከማገድ የደረሰ እርምጃ የተወሰደባቸውም አሉ፡፡
የነዳጅ መቅጃ ማሽኖቻቸውን ቴክኒካዊ በሆነ መንገድ ሆን ብለው ሊትር ቀንሰው እንዲቀዱ ማድረጋቸውን ባደረግኩት ፍተሻ ደርሼበታለሁ ሲል የነዳጅ ግብይትን የሚቆጣጠረው የከተማዋ ንግድ ቢሮ ነግሮናል፡፡
በዚህም በአዲስ አበባ ካሉት 133 ማደያዎች ከቅሸባ ነፃ የሆኑት 42 ብቻ ናቸው፡፡
91ዱ በዚህ ቅሸባ በተባለው ሊትርን የማጉደል ተግባር ሲፈፅሙ ተገኝተው ከመካከላቸው 64ቱ በማስጠንቀቂያ ታልፈዋል፤21ማደያዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፤3 ማደያዎች ክስ ተመስርቶባቸዋል፤የተቀሩት 3ቱ ከስራው ታግደዋል ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....
ምንታምር ጸጋው
_edited.jpg)




Comments