top of page

በአትላንቲክ ውቅያኖስ የገባችበት የጠፋውን ቱሪስቶች መጓጓዥ ጠላቂ ጀልባ ለማግኘት ሰፊ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ

ሰኔ 13፣2015


በአትላንቲክ ውቅያኖስ የገባችበት የጠፋውን ቱሪስቶች መጓጓዥ ጠላቂ ጀልባ ለማግኘት ሰፊ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ፡፡


ጠላቂዋ ጀልባ ከትናንት በስቲያ አንስቶ ግንኙነቷ መቋረጡን CNN በድረ ገጹ ፅፏል፡፡


ጠላቂዋ ጀልባ ቱሪስቶችን እና ተመራማሪዎችን ታይታኒክ መርከብ ወደ ሰጠመችበት ስፍራ በማጓጓዝ የምትታወቅ ነች ተብሏል፡፡


ግዙፏ መርከብ ታይታኒክ የሰመጠችው ከ111 ዓመታት በፊት እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡


ወደዚያው ቱሪስቶችን እና ተመራማሪዎችን የምታጓጉዘው ጠላቂ ጀልባ 5 ሰዎችን እንዳሳፈረች ነው የገባችበት የጠፋው፡፡


የቀራት የእስትንፋስ መደገፊያ /ኦክስጂን/ ከ4 ቀናት ያልበለጠ በመሆኑ ፍለጋው ከጊዜም ጋር እሽቅድምደፍም ውስጥ የተገባበት ነው ተብሏል፡፡


ባሕር ጠላቂ መርከቦች ፣ አውሮፕላኖች እና ሄሌኮፕተሮች የተሰለፉበት ታላቅ የነፍስ አድን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የካናዳ እና የአሜሪካ የባህር ሀይል ሹሞች ተናግረዋል፡፡የኔነህ ከበደየሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Kommentare


bottom of page