top of page

በአትላቲክ ውቅያኖስ የገባችበት ጠፍቶ የሰነበተችው ጠላቂ ጀልባ አሳፍራቸው የነበሩ 5 ሰዎች መሞታቸው ተረጋገጠ

ሰኔ 16፣2015


በአትላቲክውቅያኖስ የገባችበት ጠፍቶ የሰነበተችው ጠላቂ ጀልባ አሳፍራቸው የነበሩ 5 ሰዎች መሞታቸው ተረጋገጠ፡፡


የጀልባዋስብርባሪ እንደተገኘ ቢቢሲ አውርቷል፡፡


ባህርጠለቋ ጀልባ በተለይም ከ111 ዓመታት በፊት ከበረዶ ቋጥኝ ጋር ተላትማ የሰጠመችዋ ታይታኒክ መርከብ ስብርባሪ ወደሚገኝበት ስፍራ ጎብኚዎችን እና ተመራማሪዎችን በማጓጓዝ ትታወቅ ነበር፡፡


አሁንራሷ ባህር ጠለቋ ጀልባ የታይታኒክ ዕጣ ተጋሪ ሆናለች ተብሏል፡፡


የባህርጠለቋ ጀልባ ስብርባሪ የታይታኒክ ቅሪት ካረፈበት በ500 ሜትር ገደማ ርቀት መገኘቱ ታውቋል፡፡


ካለፈውእሁድ አንስቶ ግንኙነት አቋርጣ የሰነበተችውን ባህር ጠላቂ ጀልባ ለመፈለግ እና ተሳፋሪዎቿን በሕይወት ለማትረፍ ታላቅ ጥረት ሲደረግ መሰንበቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡የኔነህከበደየሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page