በአበባ እርሻዎች ጥቅም ላይ የሚውሉ ጸረ ተባይ ኬሚካሎች
- Jun 10
- 2 min read
ሰኔ 3/2018
በአበባ እርሻዎች ጥቅም ላይ የሚውሉ ጸረ ተባይ ኬሚካሎች አካባቢን ለብክለት በዛ የሚሰሩ ሰራተኞችንም ለጤና እክል የሚዳርጉ መሆናቸው ይነገራል፡፡
የኬሚካል ርጭቱን ለማቆም ይረዳ ዘንድ በእርሻው የሚከሰቱ ጎጂ ነፍሳትን ተመግበው የሚያስወግዱ ጎጂ ያልሆኑ ነፍሳትን እዚሁ በሀገር ቤት ማራባት ተችሏል ተብሏል፡፡
ቆቃ የሚገኝ አንድ የአበባ እርሻ ልማት ድርጅት እነዚህን ጠቃሚ የሆኑ ነብሳት እዚሁ በማራባት የውጭ ምንዛሪን ማስቀረት እና በጉዞ መዘግየት ይደርስ የነበረውን ተፅዕኖ መቀነስ መቻሉ ተጠቅሷል፡፡
በአበባ እርሻ ላይ የሚከሰቱ ተባዮችን ለመከላከል የሚረጩ ኬሚካሎች በአካባቢ ደህንንት ላይ ጉዳት እያስከተሉ እንደሆነ በተለያየ ጊዜ ይነገራል።
በእርሻዎቹ የሚሠሩ ሰራተኞች ደህንነትም በእነዚሁ ኬሚካሎች ምክንያት ለአደጋ መጋለጡን የተለያዩ ወገኖች ፤ በተለያየ ጊዜ ሲያነሱ ይሰማል።
ተመሣሣይ የደህንነት ስጋት የአበባ ምርት ገዝተው በሚጠቀሙ ሀገራት ዘንድ እንዳለ የሚናገሩት የኢትዮጵያ አበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ፤ አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ወጪውም ቀላል እንዳልሆነ ያነሳሉ።

እነዚህን ሁሉ ችግሮች ለማስቀረት እንደ መፍትሄ የተወሰደው በአበባ እርሻ ላይ የሚከሰቱ ጎጂ የሆኑ ነፍሳት ጎጂ ባልሆኑ ሌሎች ነፍሳት እንዲበሉ የማድረግ አማራጭ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
’’ሬድ ፎክስ’’ የተሰኘና በቆቃ የሚገኝ የአበባ እርሻ ልማት ድርጅት ከተወሰኑ ዓመት በፊት እነዚህን ጠቃሚ የሆኑ ነፍሳት ከውጪ በማስመጣት ጎጂ የሆኑትን እንዲመገቡ ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል፡፡
አሁን ደግሞ ድርጅቱ በራሱ የአበባ እርሻ ልማት ውስጥ ጠቃሚ የሆኑትን ነፍሳት ማራባት መጀመሩን ነግረውናል።
የሬድ ፎክስ የአበባ እርሻ ልማት ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ዮርዳኖስ ጀማል በበከሉላቸው በአመት እስከ ግማሽ ሚሊየን የሚሆኑ ጠቃሚ ነፍሳትን ድርጅታቸው ለማምረት ማቀዱን አመልክተዋል።
ድርጅቱ ነፍሳቱን ከውጪ ሲያስገባ የተለያዩ ችግሮች ይገጥሙት እንደነበርም ወይዘሮ ዮርዳኖስ ተናግረዋል።
የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፉ ወደ ስን ህይወታዊ የተባይ መከላከል ሥርዓት እየገባ ነው የሚሉት አቶ ቴዎድሮስ በበኩላቸው ፤የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂውን ያስተዋወቀው ሮድ ፎክስ ኢትዮጵያ እስከ 2500 የሚደርሱ ሠራተኞች አሉት የተባለ ሲሆን እስከ 10 ሚሊየን ዩሮ የውጭ ምንዛሪ በዓመት እንደሚያስገኝ ተነግሯል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i





Comments