top of page

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚፈጠሩ ቀውሶች የመድኃኒት አቅርቦትና ግዢ ስርዓቱን እንዳያስተጓጉል አለም አቀፍ አምራቾች እና አቅራቢዎች በጋራ መስራት አለባቸው ተባለ።

  • Apr 28
  • 1 min read

ሚያዝያ 20/2018

 

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚፈጠሩ ቀውሶች የመድኃኒት አቅርቦትና ግዢ ስርዓቱን እንዳያስተጓጉል አለም አቀፍ አምራቾች እና አቅራቢዎች በጋራ መስራት አለባቸው ተባለ።

 

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 5ኛውን ዓለም አቀፍ የመድኃኒት አቅራቢዎች ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ  እያካሄደ ነው።

 

ጦርነት ፣ ወረርሽኞች ተጽዕኖ ከሚያሳድርባቸው ዘርፎች አንዱ የመድኃኒት አቅርቦት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩ  አብዱልቃድር ጋልገሎ  (ዶ/ር) ተናግረዋል።

 

ኢትዮጵያ በፋርማሱቲካል ኢንደስትሪ ዘርፍ ከአፍሪካ እያደገ የመጣ የገበያ ስርአት ዘርግታለች ብለዋል።

 

የመድኃኒት አቅርቦት እና ስርጭት ለማቀላጠፍ አዳዲስና የዲጂታል አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

 

ሀገሪቱ ለመድኃኒትና ህክምና ግብአት ዘርፋ ምርት  ልዩ ትኩረት በመስጠቷ የቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በመገንባት አምራቾች ገብተው እየሰሩ ለሀገርቤት የመድኃኒት አቅርቦቱ ላይ እየተሳተፋ ነው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የግል መድኃኒት አምራቾች ማህበር ፕሬዝዳንቱ ዶ/ተፈሪ ታደሰ ናቸው።

 

በተጨማሪም ለሀገር ውስጥ አምራቾች የተለያዩ ማበረታቻዎች በማቅረብ የሀገር ቤት የመድኃኒት ምርቱ መጠን ከሶስት አመታት በፊት ከነበረበት 8 በመቶ አሁን ላይ ወደ 44 በመቶ እንዲጨምር ማድረጉን ጠቅሰዋል።

 

የመድኃኒት እና ህክምና ግብአት ምርት ላይ የግል አለምአቀፍ አምራቾች በስፋት እንዲሳተፋ የተለያዩ ማበረታቻዎች እየተደረጉ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።

 

አለም አቀፍ ቀውሶች ሲፈጠሩ የጤናው ዘርፍ ቀዳሚ ተጎጂ ይሆናል ያሉት ሚኒስትሯ የህክምና ግብአት እና መድኃኒት አቅርቦት እንዳይስተጓጎል አቅራቢዎች በጋራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።

 

ባለፈው በጀት ዓመት ከ68.4 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና መሳሪያዎች ለተቋማት መሰራጨቱ በኮንፍረንሱ ላይ በቀረበ ሪፖርት ተነግሯል።


ምህረት ስዩም

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page