በሀገሪቱ የቀጠለው ግጭት እና አለመረጋጋት ለንጹሃ መሞት፣ መቁሰል ንብረት መውደም እና መፈናቀል ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል ተብሏል፡፡
በተለይም ግጭት ባለባቸው በኦሮሚያ፣ አማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በታጣቂዎች በሚፈፀም ጥቃት እና መንግስት ያንን ለመከላከል አልያም ለፍትህ ለማቅረብ በሚደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ንፁሃን እየሞቱ እና እየተጎዱ መሆኑን መንግስታዊው የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪው ኢሰመኮ ተናግሯል፡፡
በግጭቶች መካከል ከሚገደሉት፣ ከሚቆስሉት፣ ከሚፈናቀሉት እና ንብረታቸው ከወደመባቸው ሰዎች ባሻገር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው ተብሏል፡፡
በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን ብቻ በትምህርት ገበታ ላይ ላይ መኖር ሲገባቸው ከ4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በግጭት ምክንያት ሳይማሩ ቀርተዋል ሲል ኮሚሽኑ አስረድቷል፡፡
በግጭቱ የወደሙ የጤና ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ገበሬዎች መተዳደሪያቸው የሆነውን የእርሻ ስራ እንዳይሰሩ አድርጓል ብሏል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments