በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ቦታ ይዘው እየሰሩ ያሉ እና አዲስ ለመግባት በሂደት ላይ የሚገኙ ባለሃብቶች የፀጥታ ችግር ተጽዕኖ እያሳደረባቸው ነው ተባለ።
በኢንዱስትሪ ፓርኩ ገብቶ ስራ ለመጀመር የማምረቻ ማሽኖችን ሲያጓጉዝ የነበረ አንድ የህንድ ኩባንያ በዚሁ የፀጥታ ችግር ምክንያት በየአካባቢው መስተጓጎል እንደገጠመው ሠምተናል።
በፓርኩ ካሉ ስምንት የማምረቻ ሼዶች አምስቱ በባለሃብቶች መያዛቸውን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የማርኬቲንግ፤ ፕሮሞሽን እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ ነግረውናል።
Comentarios