top of page

በሚቀጥሉት 10 ቀናት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተናገረ

  • 5 days ago
  • 1 min read

የካቲት 24/2018


በሚቀጥሉት 10 ቀናት አዲስ አበባን ጨምሮ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡


አሁን ያለንበት የየካቲት ወርን ጨምሮ እስከ ግንቦት ድረስ በሚዘልቀው የበልግ ወቅት ሰሞኑን እተስተዋለ ያለው የአየር ሁኔታ ለውጥ የሚጠበቅ ነው ብሏል ኢንስቲትዩቱ፡፡


በዚህ ወቀት የደቡብ አጋማሽ የሃገሪቱ ክፍል ማለትም ሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣የጉጂና ቦረና ዞኖች፣የሲዳማ ክልል ዞኖች፣የደቡብና ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች እስከ 55 በመቶ የሚሆነውን የዝናብ መጠን የሚያገኙበት ዋንኛ የዝናብ ወቅታቸው ነው፡፡


በተጨማሪም የደቡብና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፣የምስራቅ አማራ ዞኖች፣የምስራቅ የሃገሪቱ አካባቢዎች፣አዲስ አበባና የመካከለኛው ኢትዮጵያ ክፍሎች ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው መሆኑንና ከሰሞኑም ከከባድ እስከ ቀላል የዝናብ መጠን መመዝገቡን በኢንስቲትዩቱ የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ምክር አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመን ተናግረዋል፡፡



በመጪዎቹ 10 ቀናትም በእነዚህ በተጠቀሱት አካባቢዎችና በአዲስ አበባ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል ያሉት ሃላፊው የዝናብ መጠኑ የእርሻ ስራዎችንና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ለመከወን የተመቸ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡


በሌላ በኩል የበልግ ወቅት የቀኑ ሙቀት ከፍተኛ የሚሆንባቸው አካባቢዎችም አሉ ተብሏል፡፡


ባለፊት ቀናት በጋምቤላ፣በሰመራ፣በቋራ፣በሰመራ፣በቀብሪ ዳሃርና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 41 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፤በእነዚህ አካባቢዎች መበጪዎቹ ቀናትም ተመሳሳይ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር እንደሚጠበቅና፤የዝናቡ መጠን ለወቅቱ ተስማሚና ምንም ጉዳት እንደማያስከትል ከኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…


ምንታምር ፀጋው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page